ወደ ሞት የሚነዱትን ታደግ፤ የሚገደሉትንም መዋረዳቸውን ቸል አትበል።
ወደ ሞት የሚነዱትን ታደጋቸው፤ እየተጐተቱ ለዕርድ የሚሄዱትን አድናቸው።
ወደ ሞት የሚነዱትን ታደግ፥ ለመታረድ የተወሰነባቸውን አድን።
በግፍ ወደ ሞት የሚወሰዱትን ሰዎች ታደግ፤ ለመገደል እያዳፉ ከሚወስዱአቸው ሰዎች እጅ አድን።
የኀጢአተኞችን መንጋጋ ሰበርሁ፥ የነጠቁትንም ከጥርሳቸው ውስጥ አስጣልሁ።
“ኑ ከሕዝብ ለይተን እናጥፋቸው፥ ከእንግዲህም ወዲህ የእስራኤልን ስም አያስቡ” አሉ።
እልልታን የሚያውቅ ሕዝብ ብፁዕ ነው፤ አቤቱ፥ በፊትህ ብርሃን ይሄዳሉ።
ጳውሎስም፥ “በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ፤ ሁላችንም ከዚህ አለን” ብሎ በታላቅ ቃል ጮኸ።
አረማውያንም ሁሉ የምኵራቡን አለቃ ሶስቴንስን ይዘው በሸንጎ ፊት ደበደቡት፤ የእርሱም ነገር ጋልዮስን ምንም አላሳዘነውም።
እጅግም በታወኩ ጊዜ ጳውሎስን እንዳይነጥቁት የሻለቃው ፈራና መጥተው ከመካከላቸው አውጥተው ወደ ወታደሮች ሰፈር ይወስዱት ዘንድ ወታደሮቹን አዘዘ።