Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 23:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እጅ​ግም በታ​ወኩ ጊዜ ጳው​ሎ​ስን እን​ዳ​ይ​ነ​ጥ​ቁት የሻ​ለ​ቃው ፈራና መጥ​ተው ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አው​ጥ​ተው ወደ ወታ​ደ​ሮች ሰፈር ይወ​ስ​ዱት ዘንድ ወታ​ደ​ሮ​ቹን አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ጠቡ ከማየሉ የተነሣም አዛዡ ጳውሎስን እንዳይገነጣጥሉት ፈራ፤ ስለዚህ ወታደሮቹ ወርደው ከመካከላቸው ነጥቀው ወደ ጦሩ ሰፈር እንዲያስገቡት አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ብዙ ጥልም በሆነ ጊዜ የሻለቃው ጳውሎስን እንዳይገነጣጥሉት ፈርቶ ጭፍሮቹ ወርደው ከመካከላቸው እንዲነጥቁት ወደ ሰፈሩም እንዲያገቡት አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ጠቡ እየከረረ ስለ ሄደ ሰዎቹ ጳውሎስን እንዳይቦጫጭቁት ፈርቶ አዛዡ “ውረዱና ጳውሎስን ከሰዎቹ መካከል ነጥቃችሁ አምጡ! ወደ ጦሩ ሰፈርም ውሰዱት!” በማለት ወታደሮቹን አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ብዙ ጥልም በሆነ ጊዜ የሻለቃው ጳውሎስን እንዳይገነጣጥሉት ፈርቶ ጭፍሮቹ ወርደው ከመካከላቸው እንዲነጥቁት ወደ ሰፈሩም እንዲያገቡት አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 23:10
16 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ፤ በእውነትም ላይ አትዋሹ።


ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤


የሻ​ለ​ቃው የሚ​ጮ​ሁ​በት ስለ ምን እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ ወደ ወታ​ደ​ሮች ሰፈር እን​ዲ​ያ​ገ​ቡ​ትና እየ​ገ​ረፉ የሠ​ራ​ውን እን​ዲ​መ​ረ​ም​ሩት አዘዘ።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ከእ​ርሱ ጋር ይሄዱ ዘንድ ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ትተው እነ​ርሱ ወደ ሰፈር ተመ​ለሱ።


ይህን ሰው አይ​ሁድ ያዙት፤ ሊገ​ድ​ሉ​ትም ፈለጉ፤ ከወ​ታ​ደ​ሮ​ችም ጋር ተከ​ላ​ከ​ል​ሁ​ለት፥ የሮም ሰው መሆ​ኑ​ንም ዐውቄ አዳ​ን​ሁት።


የጳ​ው​ሎ​ስም የእ​ኅቱ ልጅ ምክ​ራ​ቸ​ውን በሰማ ጊዜ ሄዶ ወደ ወታ​ደ​ሮች ሰፈር ገባና ለጳ​ው​ሎስ ነገ​ረው።


የሕዝቤን ሥጋ በልታችኋል፥ ቁርበታቸውንም ገፍፋችኋቸዋል፥ አጥንታቸውንም ሰብራችኋል፥ ለአፍላል እንደሚሆን ሥጋ ለድስትም እንደሚሆን ሙዳ ቈራረጣችኋቸው።


ነፍ​ሴን እንደ አን​በሳ እን​ዳ​ይ​ነ​ጥ​ቋት፥ የሚ​ያ​ድ​ንና የሚ​ታ​ደግ ሳይ​ኖር።


ወደ ሰፈ​ርም በደ​ረሰ ጊዜ ጳው​ሎስ ሻለ​ቃ​ውን፥ “ላነ​ጋ​ግ​ርህ ትፈ​ቅ​ድ​ል​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ሻለ​ቃ​ውም፥ “የጽ​ርዕ ቋንቋ ታው​ቃ​ለ​ህን?” አለው።


በምን ምክ​ን​ያ​ትም እን​ደ​ሚ​ከ​ሱት በደ​ሉን አውቅ ዘንድ ወደ ሸንጎ አቅ​ርቤ መረ​መ​ር​ሁት።


በመ​ን​ገድ ዘወ​ትር መከራ እቀ​በል ነበር፤ በወ​ን​ዝም መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ ወን​በ​ዴ​ዎ​ችም አሠ​ቃ​ዩኝ፤ ዘመ​ዶ​ችም አስ​ጨ​ነ​ቁኝ፤ አሕ​ዛብ መከራ አጸ​ኑ​ብኝ፤ በከ​ተማ መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ በበ​ረ​ሃም መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ በባ​ሕ​ርም መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ ሐሰ​ተ​ኞች መም​ህ​ራን መከራ አጸ​ኑ​ብኝ።


ነገር ግን የሻ​ለ​ቃው ሉስ​ዮስ መጥቶ በብዙ ጭንቅ ከእ​ጃ​ችን ነጥቆ ወደ አንተ ላከው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios