ምሳሌ 23:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም ድሃ ስትሆን ከባለጠጋ ጋር አትወዳደር። በዐሳብህም ራቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሀብት ለማግኘት ስትል ራስህን አታድክም፤ ሐሳብህን የመግታት ጥበብ ይኑርህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሀብታም ለመሆን አትድከም፥ የገዛ ራስህን ማስተዋል ተው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመበልጸግ አትድከም፤ ከዚህ ዐይነት ስግብግብነት ለመራቅ ጥበበኛ ሁን፤ |
መማለጃን የሚቀበል ራሱን ያጠፋል፤ መማለጃ መቀበልን የሚጠላ ግን ይድናል። በምጽዋትና በእምነት ኀጢአት ይሰረያል። እግዚአብሔርንም በመፍራት ክፉ ሁሉ ይወገዳል።
የሰዎቻችሁም ሬሳ እንደ ጕድፍ በእርሻ ላይ፥ ማንም እንደማይሰበስበው ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል።
የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘለዓለም ሕይወት ለሚኖር መብል ሥሩ እንጂ ለሚጠፋው መብል አይደለም፤ ይህን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”
ወንድሞቻችን፥ እና ዐዋቂዎች ነን እንዳትሉ ይህን ምሥጢር ልታውቁ እወዳለሁ፦ አሕዛብ ሁሉ እስኪገቡ ድረስ ከእስራኤል እኩሌቶችን የልብ ድንቍርና አግኝቶአቸዋልና።
እርስ በርሳችሁም በአንድ ዐሳብ ተስማሙ፤ ትዕቢትን ግን አታስቡ፤ ራሱን የሚያዋርደውንም ሰው ምሰሉ፤ እና ዐዋቆች ነን አትበሉ።