ምሳሌ 23:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቶችህ ያኖሩትን የድንበር ምልክት አታፍልስ፤ ወደ ድሃ አደጎች እርሻም አትግባ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጥንቱን የወሰን ምልክት አታፋልስ፤ አባት የሌላቸውንም ልጆች መሬት አትግፋ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፍልስ፥ ወደ ድሀ አደጎች እርሻ አትግባ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቈየውን የወሰን ምልክት አትለውጥ፤ እንዲሁም አባትና እናት የሌላቸውን ልጆች መሬት አትቀማ፤ |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ፤ የተነጠቀውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ፤ መጻተኛውንና ድሃአደጉን፥ ባልቴቲቱንም አትበድሉ፤ አታምፁባቸውም፤ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ።
መጻተኛውንና ድሃአደጉን፥ መበለቲቱንም ባትገፉ፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታፈስሱ፥ ክፉም ሊሆንባችሁ እንግዶችን አማልክት ባትከተሉ፤
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር፤ በምትካፈላት ርስትህ አባቶችህ የተከሉትን የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አትንቀል።
ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።