ምሳሌ 22:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱን በልብህ ብትጠብቅ፥ በከንፈሮችህ በአንድነት ደስ ያሰኙሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በልብህ ስትጠብቃቸው፣ ሁሉም በከንፈሮችህ ላይ የተዘጋጁ ሲሆኑ ደስ ይላልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱን በውስጥህ ብትጠብቅ፥ በከንፈሮችህም ላይ የተዘጋጁ ቢሆኑ፥ አስደሳች ነገር ይሆንልሃልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘወትር ብታስታውሳቸውና ብትጠቀምባቸው ደስ ይሉሃል፤ |
ቃልህ ተገኝቶአል፤ እኔም በልችዋለሁ፤ አቤቱ! የሠራዊት አምላክ ሆይ! ቃልህን የከዱ ሰዎችን አጥፋቸው፤ ስምህ በእኔ ላይ ተጠርትዋልና፥ ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ።
ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል።
በውኑ እንግዲህ በስሙ እናምን ዘንድ የከንፈሮቻችን ፍሬ የሚሆን የምስጋና መሥዋዕትን በየጊዜው ለእግዚአብሔር ልናቀርብ አይገባንምን?