Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 16:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ጠቢብን ሰዎች ዐዋቂ ይሉታል፥ ነገሩም ጣፋጭ የሆነውን እጅግ ያደምጡታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ልባቸው ጠቢብ የሆነ አስተዋዮች ይባላሉ፤ ደስ የሚያሰኙ ቃላትም ዕውቀትን ያዳብራሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ልቡ ጠቢብ የሆነ አስተዋይ ይባላል፥ በከንፈሩም ጣፋጭ የሆነ ትምህርትን ያበዛል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በአስተሳሰብ መብሰል ጥበበኛነትን ያመለክታል፤ ጣዕም ባለው አነጋገር መናገር ሌሎችን ያስተምራል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 16:21
18 Referencias Cruzadas  

የም​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አውቅ ዘንድ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጥ​በብ ምላ​ስን ሰጥ​ቶ​ኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነ​ቃ​ኛል፤ ለመ​ስ​ማ​ትም ጆሮን ሰጥ​ቶ​ኛል።


የጠቢባን ከንፈሮች በዕውቀት የታሰሩ ናቸው፤ የሰነፎች ልብ ግን የጸና አይደለም።


ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ፥ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።


ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም መል​ሰው፥ “ያ ሰው እንደ ተና​ገ​ረው ያለ ከቶ ሰው አል​ተ​ና​ገ​ረም” አሉ​አ​ቸው።


ሁሉም የን​ግ​ግ​ሩን መከ​ና​ወን መሰ​ከ​ሩ​ለት፤ የአ​ን​ደ​በ​ቱ​ንም ቅል​ጥ​ፍና እያ​ደ​ነቁ፥ “ይህ የዮ​ሴፍ ልጅ አይ​ደ​ለ​ምን?” ይሉ ነበር።


ሰባ​ኪ​ውም ያማ​ረ​ውን በቅ​ንም የተ​ጻ​ፈ​ውን እው​ነ​ተ​ኛ​ው​ንም ቃል መር​ምሮ ለማ​ግ​ኘት ፈለገ።


ልጄ ሆይ፥ ልብህ ጠቢብ ይሁን ልቤን ደግሞ ደስ ያሰኛል፤


በልቡ ጠቢብ የሆነ ትእዛዝን ይቀበላል፤ በከንፈሩ የማይታገሥ ግን በመሰናክል ይወድቃል።


ስለ​ዚህ ምድር ብት​ነ​ዋ​ወጥ፥ ተራ​ሮ​ችም ወደ ባሕር ልብ ቢፈ​ልሱ አን​ፈ​ራም።


እነሆ፥ እኔ እንደ ቃልህ አድ​ር​ጌ​ል​ሃ​ለሁ፤ እነ​ሆም፥ ማንም የሚ​መ​ስ​ልህ ከአ​ንተ በፊት እን​ደ​ሌለ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ እን​ዳ​ይ​ነሣ አድ​ርጌ ጥበ​በ​ኛና አስ​ተ​ዋይ ልቡና ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።


መታ​ዘ​ዛ​ች​ሁም በሁሉ ዘንድ ተሰ​ም​ቶ​አል፤ እኔም በእ​ና​ንተ ደስ ይለ​ናል፤ ለመ​ል​ካም ነገር ጠቢ​ባን፥ ለክፉ ነገ​ርም የዋ​ሃን እን​ድ​ት​ሆኑ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “አባት ሆይ! የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።


በጎ ዐሳብ ገንዘብ ላደረጋት ሰው የሕይወት ምንጭ ናት፤ የሰነፎች ትምህርት ግን ክፉ ናት።


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤ​ፍ​ሬም ምን​ድን ነው? እኔ አደ​ከ​ም​ሁት፤ አጸ​ና​ሁ​ትም፤ እኔ እንደ ተወ​ደደ አበባ አፈ​ራ​ዋ​ለሁ፤ ፍሬ​ህም በእኔ ዘንድ ይገ​ኛል።


ብልህ ሰው ከከንፈሩ ጥበብን ያወጣል፤ አእምሮ የጐደለውንም ሰው በበትር ይመታል።


ሰነፍ ሰው በመሳቁ ክፉን ይሠራል፤ ጥበብ ግን ለሰው ዕውቀትን ትወልዳለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios