ምሳሌ 21:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኃጥኣን መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ በክፋት ያቀርቡታልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክፉ ሰው መሥዋዕት አስጸያፊ ነው፤ በክፉ ዐላማ ሲያቀርብማ የቱን ያህል አስከፊ ይሆን! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የክፉዎች መሥዋዕት አስጸያፊ ነው፥ ይልቁንም በክፉ አሳብ ሲያቀርቡት አስጸያፊ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐመፀኞች የሚያቀርቡት መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ አጸያፊ ነው፤ በተለይም በክፉ አሳብ ተነሣሥተው የሚያቀርቡለት መሥዋዕት የበለጠ አጸያፊ ነው። |
ወደ እግዚአብሔር ቤት በምትሄድበት ጊዜ እግርህን ጠብቅ፤ የጠቢባንንም ትምህርት ለመስማት ቅረብ፤ ዳግመኛም ከሰነፎች ስጦታ መሥዋዕት አድርገህ ከመቀበል ተጠበቅ፤ እነርሱ መልካም ለመሥራት ዐዋቂዎች አይደሉምና።
በሬን የሚሠዋልኝ ኃጥእ ውሻን እንደሚያርድልኝ ነው፤ የእህልን ቍርባን የሚያቀርብም የእሪያን ደም እንደሚያቀርብ ነው፤ ዕጣንንም ለመታሰቢያ የሚያጥን አምላክን እንደሚፀርፍ ነው፤ እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኵሰታቸው ደስ ይላታል።
ስለ ምንስ ከሳባ ዕጣንን፥ ከሩቅም ሀገር ቀረፋን ታቀርቡልኛላችሁ? የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን አልቀበለውም፤ ቍርባናችሁም ደስ አያሰኘኝም።
ሙሴም እጅግ አዘነ፤ እግዚአብሔርንም አለው፥ “ወደ መሥዋዕታቸው አትመልከት፤ እኔ ከእነርሱ አንዳችም ተመኝቼ አልወሰድሁም፤ ከእነርሱም አንድ ሰው አልበደልሁም።”
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።