ምሳሌ 21:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው ሁሉ ለራሱ ጻድቅ መስሎ ይታያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያቀናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሰው መንገዱ ሁሉ ቀና ይመስለዋል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት የቀናች ትመስለዋለች፥ ጌታ ግን ልብን ይመዝናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ይመስለዋል፤ እግዚአብሔር ግን የልብን ሐሳብ ይመዝናል። |
እነሆ፥ ይህን አላውቅም ብትል፥ እግዚአብሔር የሁሉን ልብ እንዲያውቅ ዕወቅ። ለሁሉ እስትንፋስን የፈጠረ እርሱ ሁሉን ያውቃል። ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፍለዋል።
እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱና፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ፤ ኵላሊትንም እፈትናለሁ።”
እርሱም፥ “እናንተስ ለሰው ይምሰል ትመጻደቃላችሁ፤ እግዚአብሔርም ልቡናችሁን ያውቃል፤ በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ዘንድ የተናቀ ይሆናልና።
ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።
እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፥ “ፊቱን፥ የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንደሚያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው።