እንዲህም በሉ፦ እነሆ አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን ነው። በፊቴ በሚሄደው እጅ መንሻ እታረቀዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ምናልባት ይራራልኛል፤ ፊቱንም አያለሁ ብሎአልና።”
ምሳሌ 21:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስውር ያለ ስጦታ ቍጣን ይመልሳል፥ ስጦታን የሚሸልግ ግን ጽኑ ቍጣን ያስነሣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በስውር የተደረገ ስጦታ ቍጣን ያበርዳል፤ በጕያ የተሸሸገ እጅ መንሻም ታላቅ ቍጣን ጸጥ ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስጦታ በስውር ቁጣን ታጠፋለች፥ የብብትም ውስጥ ጉቦ ጽኑ ቁጣን ታበርዳለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተቈጣ ሰው ስጦታ በድብቅ ሲቀርብለት ንዴቱ ይበርድለታል፤ በምሥጢር የሚሰጥ እጅ መንሻ ቊጣን ያበርዳል። |
እንዲህም በሉ፦ እነሆ አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን ነው። በፊቴ በሚሄደው እጅ መንሻ እታረቀዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ምናልባት ይራራልኛል፤ ፊቱንም አያለሁ ብሎአልና።”
አባታቸው እስራኤልም እንዲህ አላቸው፥ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ ፤ ከምድሩ ፍሬ በዓይበታችሁ ይዛችሁ ሂዱ፤ ለዚያም ሰው እጅ መንሻ፥ ጥቂት በለሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ዕጣን፥ ተምር፥ ለውዝ ውሰዱ።
ዳዊትም ያመጣችውን ከእጅዋ ተቀብሎ፥ “በሰላም ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ እነሆ፥ ቃልሽን እንደ ሰማሁ፥ ፊትሽንም እንዳከበርሁ ተመልከቺ” አላት።