የኀጢአተኛ ነፍስ በአንድ ሰው እንኳ ይቅር አትባልም።
ክፉ ሰው ክፋትን አጥብቆ ይመኛል፤ ባልንጀራውም ከርሱ ዘንድ ርኅራኄን አያገኝም።
የኀጥእ ነፍስ ክፉን ትመኛለች፥ በፊቱም ባልንጀራው ሞገስን አያገኝም።
ዐመፀኞች ዘወትር ክፋትን ማድረግ ይወዳሉ፤ ለማንም ሰው ርኅራኄ የላቸውም።
እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ማን ነው? በልዕልና የሚኖር።
መካኒቱን በቤቱ የሚያኖራት፥ ደስ የተሰኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት።
በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።
የኃጥኣን ምኞት ክፋት ናት። የጻድቃን ሥር ግን የጸና ነው።
ድሃውን የሚንቅ ኀጢአትን ይሠራል፤ ለድሃ የሚራራ ግን ብፁዕ ነው።
ክፉ በመሥራት ደስ ለሚላቸው ክፋትንም በመመለስ ሐሤትን ለሚያደርጉ፥
ድሃን እንዳይሰማ ጆሮውን የሚደፍን ሰው፥ እርሱ ራሱ ይጣራል፥ የሚሰማውም የለም።
ከነዝናዛ ሴት ጋር በተለሰነ ቤት ከመቀመጥ ይልቅ፥ ከቤት ውጭ በማዕዘን ላይ መቀመጥ ይሻላል።
እርሱ ተማምኖብህ ከአንተ ጋር ተቀምጦ ሳለ፥ እንደገና በወዳጅህ ላይ ክፉ አታስብ፤
እነርሱ እንደ ተመኙ እኛ ደግሞ ክፉ እንዳንመኝ እነርሱ ለእኛ ምሳሌ ሆኑልን።
ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።