እንዲህም በሉ፦ እነሆ አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን ነው። በፊቴ በሚሄደው እጅ መንሻ እታረቀዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ምናልባት ይራራልኛል፤ ፊቱንም አያለሁ ብሎአልና።”
ምሳሌ 19:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ ሰዎች በነገሥታት ፊት ያገለግላሉ፥ ነገር ግን የሰው ጽድቁና ሀብቱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ናቸው፤ ክፉ ሁሉም የሰው መዘባበቻ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙ ሰዎች በገዥ ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ያሸረግዳሉ፤ ስጦታን ከሚሰጥ ሰው ጋራ ሁሉም ወዳጅ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙ ሰዎች ለጋሱን ያቈላምጣሉ፥ ስጦታ ለሚሰጥም ሁሉ ወዳጅ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ ሰዎች የለጋሥ ሰውን ወዳጅነት ይፈልጋሉ፤ ስጦታን ለሚሰጥ ሰው ሁሉም ወዳጁ ነው። |
እንዲህም በሉ፦ እነሆ አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን ነው። በፊቴ በሚሄደው እጅ መንሻ እታረቀዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ምናልባት ይራራልኛል፤ ፊቱንም አያለሁ ብሎአልና።”
ዮሴፍም በግብፅ ምድር ላይ ገዥ ነበረ፤ እርሱም ለምድር ሕዝብ ሁሉ እህል ይሸጥ ነበር፤ የዮሴፍም ወንድሞች በመጡ ጊዜ በምድር ላይ በግንባራቸው ሰገዱለት።
ሰዎቹም በእጃቸው ያችን እጅ መንሻና ብራቸውን በእጥፍ፥ ብንያምንም ከእነርሱ ጋር ወሰዱ፤ ተነሥተውም ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዮሴፍም ፊት ቆሙ፤ ሰገዱለትም።
ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።