ምሳሌ 17:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የብልህ ሰው ፊት ዐዋቂ ነው፤ የአላዋቂ ሰው ዐይኖች ግን በምድር ዳርቻ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አስተዋይ ሰው ጥበብን ከፊቱ አይለያትም፤ የሞኝ ዐይኖች ግን እስከ ምድር ዳርቻ ይንከራተታሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአስተዋይ ፊት ጥበብ ትኖራለች፥ የሰነፍ ዐይን ግን በምድር ዳርቻ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አስተዋይ ሰው ወደ ጥበብ ያዞራል፤ የሞኝ ዐይኖች ግን በብዙ አቅጣጫ ይባዝናሉ። |
የጠቢብ ዐይኖች በራሱ ላይ ናቸውና፤ አላዋቂ ግን በጨለማ ይሄዳል፤ ደግሞ የሁለቱም መጨረሻቸው አንድ እንደ ሆነ አስተዋልሁ።
ዐዋቂዎችን ማን ያውቃቸዋል? ቃላቸውንስ መተርጐም የሚያውቅ ማን ነው? የሰው ጥበቡ ፊቱን ታበራለች፥ በፊቱም ኀፍረት የሌለው ሰው ይጠላል።
ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድድ ግን ትምህርቴ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ሆነች፥ የምናገረውም ከራሴ እንዳይደለ እርሱ ያውቃል።