Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መክብብ 8:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ዐዋ​ቂ​ዎ​ችን ማን ያው​ቃ​ቸ​ዋል? ቃላ​ቸ​ው​ንስ መተ​ር​ጐም የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው? የሰው ጥበቡ ፊቱን ታበ​ራ​ለች፥ በፊ​ቱም ኀፍ​ረት የሌ​ለው ሰው ይጠ​ላል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ነገሮችን መግለጽ የሚችል፣ እንደ ጠቢብ ያለ ሰው ማን ነው? ጥበብ የሰውን ፊት ታበራለች፤ የከበደ ገጽታውንም ትለውጣለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጠቢብን የሚመስለው? የነገሮችንስ ትርጒም የሚያውቅ ማን ነው? የሰው ጥበብ ፊቱን ታበራለች፥ የፊቱንም ድንዳኔ ትለውጣለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ጥበበኛን የሚመስለው ማነው? የነገሮችን ፍቺ የሚያውቅ ማነው? ጥበብ የሰውን ፊት ታበራለች፤ ኰስታራነትንም ትለውጣለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እንደ ጠቢብ የሆነ ሰው ማን ነው? ነገርንስ መተርጐም የሚያውቅ ማን ነው? የሰው ጥበብ ፊቱን ታበራለች፥ የፊቱንም ድፍረት ትለውጣለች።

Ver Capítulo Copiar




መክብብ 8:1
27 Referencias Cruzadas  

እነ​ር​ሱም፥ “ሕል​ምን አል​መን የሚ​ተ​ረ​ጕ​ም​ልን አጣን” አሉት። ዮሴ​ፍም አላ​ቸው፥ “ሕል​ምን የሚ​ተ​ረ​ጕም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠው አይ​ደ​ለ​ምን? እስቲ ንገ​ሩኝ፤ ሕል​ማ​ችሁ ምን​ድን ነው?”


የሞት መላ​እ​ክት ምንም ሺህ ቢሆኑ፥ በልቡ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊመ​ለስ ቢያ​ስብ፥ ኀጢ​አ​ቱን ለሰው ቢና​ገር፥ በደ​ሉ​ንም ቢገ​ልጥ፥ ከእ​ነ​ርሱ አንዱ እንኳ አይ​ገ​ድ​ለ​ውም፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የሙ​ሴን ፊት እን​ዳ​ን​ጸ​ባ​ረቀ ያዩ ነበር፤ እር​ሱም ከእ​ርሱ ጋር ሊነ​ጋ​ገር እስ​ኪ​ገባ ድረስ እንደ ገና በፊቱ መሸ​ፈኛ ያደ​ርግ ነበር።


ምሳሌንና የተሸሸገውን ነገር፥ የጠቢባንን ቃልና ዕንቈቅልሾችን ያውቃል።


የብልህ ሰው አንደበት በሰው ሁሉ ዘንድ ይመሰገናል፤ ልበ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል።


የብልህ ሰው ፊት ዐዋቂ ነው፤ የአላዋቂ ሰው ዐይኖች ግን በምድር ዳርቻ ናቸው።


ኃጥእ ሰው ያለ ኀፍረት ፊት ለፊት ይቃወማል፤ ቅን ሰው ግን መንገዱን ይረዳል።


ጠቢብ ሰው ከብርቱ ይሻላል፥ ከታላቅ ርስትም ይልቅ ዕውቀት ያለው ይበልጣል።


በፊታቸውም ተለወጠ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።


ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም ግልጥ አድ​ር​ገው ሲና​ገሩ ባዩ​አ​ቸው ጊዜ፥ ያል​ተ​ማ​ሩና መጽ​ሐ​ፍን የማ​ያ​ውቁ ሰዎች እንደ ሆኑ ዐው​ቀው አደ​ነቁ፤ ሁል​ጊ​ዜም ከኢ​የ​ሱስ ጋር እንደ ነበሩ ዐወቁ።


አሁ​ንም አቤቱ፥ ትም​ክ​ህ​ታ​ቸ​ውን ተመ​ል​ከት፤ ቃል​ህ​ንም በግ​ልጥ ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ ለባ​ሮ​ችህ ስጣ​ቸው።


በሸ​ን​ጎም ተቀ​ም​ጠው የነ​በ​ሩት ሁሉ ትኩር ብለው ተመ​ለ​ከ​ቱት፤ ፊቱ​ንም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ፊት ሆኖ አዩት።


ስለ​ዚህ ቍጣን ስለ መፍ​ራት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ስለ ሕሊና ደግሞ መገ​ዛት ግድ ነው።


ለእ​ኔም፦ ቃልን እን​ዲ​ሰ​ጠኝ፥ አፌ​ንም ከፍቼ የወ​ን​ጌ​ልን ምሥ​ጢር በግ​ልጥ እን​ድ​ና​ገር ጸል​ዩ​ልኝ።


ፊቱ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ውን፥ የሽ​ማ​ግ​ሌ​ው​ንም ፊት የማ​ያ​ፍ​ረ​ውን፥ ሕፃ​ኑ​ንም የማ​ይ​ም​ረ​ውን ሕዝብ ያመ​ጣ​ብ​ሃል።


ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዛብም ሁሉ እንዲሰሙት፥ ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፤ ከአንበሳ አፍም ዳንሁ።


ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos