የደማስቆ ወንዞች ባብናና ፋርፋ ከእስራኤል ውኆች ሁሉ አይሻሉምን? ሄጄስ በእነርሱ ውስጥ መጠመቅና መንጻት አይቻለኝም ኖሮአልን?” ብሎ በቍጣ ተመልሶ ሄደ።
ምሳሌ 16:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትዕግሥተኛ ሰው ከኀያል፥ ጥበብ ያለው ሰውም ሰፊ ርስት ካለው፥ በመንፈሱ የሠለጠነ ሰውም ሀገርን ከሚገዛ ሰው ይሻላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታጋሽ ሰው ከጦረኛ፣ ስሜቱን የሚገዛም ከተማን በጕልበቱ ከሚይዝ ይበልጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ ስሜቱን የሚገዛ ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኀይለኛ ከመሆን ይልቅ ታጋሽ መሆን ይሻላል፤ ብዙ ከተሞችን በጦርነት ድል ነሥቶ ከመያዝ ይልቅ ራስን መቈጣጠር ይበልጣል። |
የደማስቆ ወንዞች ባብናና ፋርፋ ከእስራኤል ውኆች ሁሉ አይሻሉምን? ሄጄስ በእነርሱ ውስጥ መጠመቅና መንጻት አይቻለኝም ኖሮአልን?” ብሎ በቍጣ ተመልሶ ሄደ።
ቍጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ ትዕግሥተኛ ሰው ግን የሆነውን ስንኳ ያጠፋል። ትዕግሥተኛ ሰው ክርክርን ያጠፋል፥ ኀጢአተኛ ሰው ግን ጠብን ፈጽሞ ያነሣል።