ምሳሌ 16:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን መፍራት በጎ ዕውቀትና ጥበብ ነው። ለሚመልስላትም የክብር መጀመሪያ ናት፥ የዋሃንንም ክብር ትከተላቸዋለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልብ ዕቅድ የሰው ነው፤ የአንደበት መልስ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የልብ መዘጋጀት ከሰው ነው፥ የምላስ መልስ ግን ከጌታ ዘንድ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው ዕቅድ ያወጣል፥ ነገር ግን ዕቅዱ በሥራ ላይ የሚውለው እግዚአብሔር ይሁን ብሎ ሲፈቅድ ብቻ ነው። |
የሰረገሎችም አለቆች ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ፥ “የእስራኤል ንጉሥ ነው” አሉ፤ ሊጋጠሙትም ከበቡት፤ ኢዮሣፍጥ ግን ጮኸ፤ እግዚአብሔርም አዳነው፤ አምላኩም ከእርሱ መለሳቸው።
ያባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ያከብር ዘንድ ይህን ነገር በንጉሡ ልብ ያኖረ፥
ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባሪያህን ጸሎት፥ ስምህንም ይፈሩ ዘንድ የሚወድዱትን የባሪያዎችህን ጸሎት ያድምጥ፤ ዛሬም ለባሪያህ አከናውንለት፤ በዚህም ሰው ፊት ምሕረትን ስጠው።” እኔም ለንጉሡ ጠጅ አሳላፊ ነበርሁ።
አንተም ትናገረዋለህ፤ ቃሌንም በአፉ ታደርገዋለህ፤ እኔ አንደበትህንና አንደበቱን አረታለሁ፤ የምታደርጉትንም አለብማችኋለሁ።