እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ባለማወቅህ በድለሃል፤ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይሆንብሃል።”
ምሳሌ 15:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉ ቦታ ናቸው፤ ክፉዎችንና ደጎችንም ይመለከታሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉም ስፍራ ናቸው፤ ክፉዎችንም ደጎችንም ነቅተው ይመለከታሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ዐይኖች በስፍራ ሁሉ ናቸው፥ ክፉዎችንና ደጎችን ይመለከታሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በየቦታው የሚደረገውን ነገር ሁሉ ያያል። መልካምም ሆነ ክፉ ድርጊትን ይመለከታል። |
እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ባለማወቅህ በድለሃል፤ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይሆንብሃል።”
ሰው በስውር ቦታ ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር በምክር ታላቅ በሥራም ብርቱ ነህ፤ ስምህ ታላቅ የሆነ፥ ኀያል፥ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ለሁሉም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ፍሬ ትሰጥ ዘንድ ዐይኖችህ በሰው ልጆች መንገድ ሁሉ ተገልጠዋል።
የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? እነዚህ ሰባቱ ደስ ብሎአቸው በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ያያሉ፣ እነዚህም በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የእግዚአብሔር ዓይኖች ናቸው።
እኛን በሚቈጣጠር በእርሱ በዐይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቈተና የተገለጠ ነው እንጂ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።