ምሳሌ 13:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቃን ለብዙ ዓመት በብልጽግና ይኖራሉ፤ ዐመፀኞች ግን ፈጥነው ይጠፋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የድኾች ዕርሻ የተትረፈረፈ ምርት ያስገኛል፤ የፍትሕ መጓደል ግን ጠራርጎ ይወስደዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በድሆች እርሻ ላይ ብዙ ሲሳይ አለ፥ ከፍርድ መጉደል የተነሣ ግን ይጠፋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የድኻ እርሻ የተትረፈረፈ ምርትን ሊያስገኝ ይችል ይሆናል። ከፍርድ መጓደል የተነሣ ግን ይጠፋል። |
ምድሩን የሚያርሳት ሰው እንጀራን ይጠግባል፤ ቦዘኔነትን የሚከተል ግን የአእምሮ ድህነትን ይሰበስባል። በወይን ግብዣ ራሱን ደስ የሚያሰኝ ሰው በሰውነቱ ውርደትን ያመጣል።
የዚያችም ከተማ ሽማግሌዎች ጊደሪቱን ይዘው ፈሳሽ ውኃ ወዳለበት ወዳልታረሰና ዘርም ወዳልተዘራበት ሽለቆ ይሄዳሉ፤ በዚያም በሸለቆው ውስጥ የጊደሪቱን ቋንጃዋን ይቈርጣሉ።