ምሳሌ 13:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብልህ ሁሉ በዕውቀት ይሠራል፤ ሰነፍ ግን ክፋቱን ይገልጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አስተዋይ ሰው ሥራውን በዕውቀት ያከናውናል፤ ሞኝ ግን ቂልነቱን ይገልጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብልህ ሁሉ በእውቀት ይሠራል፥ ሰነፍ ግን ስንፍናውን ይገልጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አስተዋይ ሰዎች ለሚሠሩት ሥራ አስቀድመው ዕቅድ ያወጣሉ፤ ማስተዋል የጐደላቸው ሰዎች ግን አላዋቂነታቸውን ይገልጣሉ። |
መታዘዛችሁም በሁሉ ዘንድ ተሰምቶአል፤ እኔም በእናንተ ደስ ይለናል፤ ለመልካም ነገር ጠቢባን፥ ለክፉ ነገርም የዋሃን እንድትሆኑ እፈልጋለሁ።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ በአእምሮ እንደ ሕፃናት አትሁኑ፤ ነገር ግን ለክፉ ነገር እንደ ሕፃናት ሁኑ፤ በዕውቀትም ፍጹማን ሁኑ።
ስለዚህም በጌታችንና በቤቱ ሁላ ክፉ ነገር እንዲመጣ ተቈርጦአልና፥ እርሱ ክፉ ሰው ስለ ሆነ ማንም ሊናገረው አይችልምና የምታደርጊውን ተመልከቺና ዕወቂ።”
በዚህ ክፉ ሰው በናባል ላይ ጌታዬ ልቡን እንዳይጥል እለምናለሁ፤ እንደ ስሙ እንዲሁ እርሱ ነው፤ ስሙ ናባል ነው፤ ስንፍናም አድሮበታል፤ እኔ ባሪያህ ግን አንተ የላክሃቸውን ብላቴኖችህን አላየሁም።