Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 14:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 በደግ ሰው ልብ ጥበብ ታድራለች፤ በአላዋቂ ሰው ልብ ግን አትታወቅም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ጥበብ በአስተዋዮች ልብ ታድራለች፤ በሞኞች መካከል እንኳ ራሷን ትገልጣለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 በአዋቂ ልብ ጥበብ ትቀመጣለች፥ በሰነፎች ውስጥ ግን አትታወቅም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 የአስተዋይ ሰው ልብ ጥበብን የተሞላ ነው፤ በሞኞች ልብ ግን ጥበብ አትታወቅም።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 14:33
10 Referencias Cruzadas  

ሰነፍ ቍጣውን በየቀኑ ይናገራል፤ ብልህ ሰው ግን ነውርን ይሰውራል።


ደግ​ሞም ሰነፍ በልቡ ፈቃ​ድና መን​ገድ በሚ​ሄድ ጊዜ አእ​ምሮ ይጐ​ድ​ለ​ዋል፥ የሚ​ያ​ስ​በ​ውም ሁሉ ሰን​ፍና ነው።


የጻድቃን ልብ ታማኝነትን ይማራል፤ የኃአጥኣን አፍ ግን ክፋትን ይመልሳል። የደጋግ ሰዎች መንገዶች በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደዱ ናቸው፥ ስለ እነርሱም ጠላቶች ወዳጆችን ይሆናሉ።


ብልህ ሁሉ በዕውቀት ይሠራል፤ ሰነፍ ግን ክፋቱን ይገልጣል።


ብልህ ሰው የጥበብ መንበር ነው፤ የሰነፎች ልብ ግን መርገምን ያገኛል።


የጠቢባን ምላስ መልካም ነገርን ታውቃለች፤ የአላዋቂዎች አፍ ግን ክፋትን ይናገራል።


ጥበብ ወደ ልብህ በመጣች ጊዜ፥ ዕውቀትም ለነፍስህ መልካምና ክብር በሆነች ጊዜ፥


ኃጥእ በክፋቱ ይወገዳል፤ በቸርነቱ የሚታመን ግን ጻድቅ ነው።


ጽድቅ ሕዝብን ከፍ ከፍ ታደርጋለች፤ ኀጢአት ግን ሕዝብን ታሳንሳለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios