እስራኤልም ሁሉ ንጉሡ እንዳልሰማቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ ለንጉሡ፥ “በዳዊት ዘንድ ምን ክፍል አለን? በእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም። እስራኤል ሆይ፥ ወደ ድንኳኖቻችሁ ተመለሱ፤ ዳዊት ሆይ፥ አሁን የራስህን ቤት ተመልከት” ብለው መለሱለት። እስራኤልም ወደየቤታቸው ተመለሱ።
ምሳሌ 13:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉ ሰው ከመሳደብ ጋር ክፋትን ይሠራል፤ ራሳቸውን የሚያውቁ ግን ብልሆች ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትዕቢት ጠብን ብቻ ያስፋፋል፤ ጥበብ ግን ምክርን በሚቀበሉ ዘንድ ትገኛለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በትዕቢት ጠብ ብቻ ይሆናል፥ ጥበብ ግን ምክርን በሚቀበሉ ዘንድ ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትዕቢት ጠብን ያመጣል፤ ምክርን መጠየቅ ግን ብልኅነት ነው። |
እስራኤልም ሁሉ ንጉሡ እንዳልሰማቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ ለንጉሡ፥ “በዳዊት ዘንድ ምን ክፍል አለን? በእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም። እስራኤል ሆይ፥ ወደ ድንኳኖቻችሁ ተመለሱ፤ ዳዊት ሆይ፥ አሁን የራስህን ቤት ተመልከት” ብለው መለሱለት። እስራኤልም ወደየቤታቸው ተመለሱ።
ኤዶምያስን በእውነት መታህ፤ ልብህንም ከፍ ከፍ አደረግህ፤ በዚያ ተመካ፤ በቤትህም ተቀመጥ፤ አንተ፥ ይሁዳም ከአንተ ጋር ትወድቁ ዘንድ ስለ ምን መከራን ትሻለህ?” ብሎ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ ላከ።
ለጻድቃን ሁልጊዜ ብርሃን ነው፤ የኃጥኣን መብራት ግን ትጠፋለች። የሐሰተኞች ነፍሳት በኀጢአት ይስታሉ። ጻድቃን ግን ይራራሉ፥ ይመጸውታሉም።
በትዕቢት ተነፍቶአል፤ አንዳችም አያውቅም፤ ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፤ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ።
ከዚያም በኋላ ያያት ሁሉ እንዲህ አለ፥ “እስራኤል ከግብፅ ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር የሆነበት ጊዜ የለም፤ የታየበትም ጊዜ የለም፤” ያም ሰው እነዚያን የላካቸውን ሰዎች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፥ “የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ በሏቸው፦ እስራኤል ከግብፅ ከወጡ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ እንዲህ የሆነበት ጊዜ አለን? እናንተ ተመካከሩበት፤ የሚበጀውንም ተነጋገሩ።”