ምሳሌ 12:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኃጥኣን ምክር ተንኮል ነው። የቅኖች አፍ ግን ይታደጋቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክፉዎች ቃል ደም ለማፍሰስ ታደባለች፤ የቅኖች ንግግር ግን ይታደጋቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የክፉ ሰዎች ቃላት ደምን ለማፍሰስ ያደባሉ፥ የቅኖች አፍ ግን ያድናቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉዎች ሰውን ለማጥፋት በንግግራቸው ያጠምዳሉ፤ የቀጥተኞች ንግግር ግን ያድናቸዋል። |
እግሮቻቸውም ለተንኮል ይሮጣሉ፤ ደምን ለማፍሰስም ይፈጥናሉ፤ ሰውን ለመግደል ይመክራሉ፤ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ በመንገዳቸው አለ።
በነጋም ጊዜ አይሁድ ተሰብስበው፥ ጳውሎስን እስኪገድሉት ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ ተስማምተው ተማማሉ።
አሁንም እናንተ ከሸንጎው ጋር ወደ ሻለቃው ሂዱና የምትመረምሩትና የምትጠይቁት አስመስላችሁ ጳውሎስን እንዲያመጣው ንገሩት፤ እኛ ግን ወደ እናንተ ከመድረሱ አስቀድሞ ልንገድለው ቈርጠናል።”
ልኮም ወደ ኢየሩሳሌም አደባባይ እንዲያስመጣውና እንዲሰጣቸው ለመኑት፤ እነርሱ ግን ወደዚያ ሄደው በመንገድ ሸምቀው ሊገድሉት ፈልገው ነበር።