ምሳሌ 12:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጽድቅ መንገድ ሕይወት አለ፥ ክፉን የሚያስቡ ሰዎች መንገዶች ግን ወደ ሞት ያወርዳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጽድቅ መንገድ ላይ ሕይወት አለ፤ በዚያ ጐዳና ላይ ሞት የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጽድቅ መንገድ ላይ ሕይወት አለ በጎዳናዋም ሞት የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እውነተኛነት የሕይወት መንገድ ነው፤ ክፋት ግን የሞት መንገድ ነው። |
ለዚህም ሕዝብ እንዲህ በል፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በፊታችሁ የሕይወትን መንገድና የሞትን መንገድ አድርጌአለሁ።
በትእዛዜም ቢሄድ፥ እውነትንም ለማድረግ ፍርዴን ቢጠብቅ፥ እርሱ ጻድቅ ነው፤ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ኀጢአትም ሞትን እንደ አነገሠችው እንዲሁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ጸጋ ጽድቅን ለዘለዓለም ሕይወት ታነግሠዋለች።
በፊትህ ሕይወትንና ሞትን፥ በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ፤
እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዝዙበት ዛሬ የምመሰክርላችሁን ቃል ሁሉ በልባችሁ አኑሩት።