ምሳሌ 11:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሐሰት እጅን በእጅ የሚመታ አይድንም፤ ጽድቅን የሚዘራ ግን የታመነ ዋጋን ያገኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ ሳይቀጣ እንደማይቀር ዕወቅ፣ ጻድቃን ግን በነጻ ይሄዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ ሰው በእርግጠኛነት ሳይቀጣ አይቀርም፥ የጻድቃን ዘር ግን ይድናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርግጥ ክፉ ሰዎች መቀጣታቸው የማይቀር ነው፤ ደጎች ግን ይድናሉ። |
ስለ ጠቡ በእሳት አቃጥለው ዘንድ ቀርቃሃና ሣርን ማን በሰጠኝ! አሁንም እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ ዛሬ አደረገ፤ እነርሱ ተቃጥለዋልና።
ለእነርሱም፥ ከእነርሱም በኋላ ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ ለዘለዓለም እንዲፈሩኝ ሌላ መንገድና ሌላ ልብ እሰጣቸዋለሁ።
ሚስቶቻቸውም ለሌሎች አማልክት ማጠናቸውን ያወቁ ሰዎች ሁሉ፥ በዚያም የቆሙ ሴቶች ሁሉ፥ በግብፅም ምድር በጳትሮስ የተቀመጡ ሕዝብ ሁሉ፥ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ለኤርምያስ መለሱለት፤ እንዲህም አሉ፦