አምላኬ ሆይ፥ ልብን እንደምትመረምር፥ ጽድቅንም እንደምትወድድ አውቃለሁ፤ እኔም በልቤ ቅንነትና በፈቃዴ ይህን ሁሉ አቅርቤአለሁ፤ አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በፈቃዱ እንዳቀረበልህ በደስታ አይቻለሁ።
ምሳሌ 11:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠማማ መንገድ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ በመንገዳቸው ፍጹማን የሆኑ ግን በፊቱ የተመረጡ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ልበ ጠማሞችን ይጸየፋል፤ በመንገዳቸው ነቀፋ በሌለባቸው ሰዎች ግን ደስ ይሰኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልበ ጠማሞች በጌታ ዘንድ አስጸያፊዎች ናቸው፥ በመንገዳቸው ፍጹማን የሆኑ ግን የተወደዱ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ልበ ጠማሞችን ይጸየፋል። ነቀፋ በሌለበት መንገድ በሚሄዱ ሰዎች ይደሰታል። |
አምላኬ ሆይ፥ ልብን እንደምትመረምር፥ ጽድቅንም እንደምትወድድ አውቃለሁ፤ እኔም በልቤ ቅንነትና በፈቃዴ ይህን ሁሉ አቅርቤአለሁ፤ አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በፈቃዱ እንዳቀረበልህ በደስታ አይቻለሁ።
የሕይወት መንገዶች ከክፉ ያርቃሉ፤ የጽድቅ ጎዳና የዘመን ብዛት ነው። ትምህርትን የሚቀበል በበጎ ይኖራል። ተግሣጽን የሚጠብቅም ብልሃተኛ ይሆናል። መንገዶቹን የሚጠብቅ ሰውነቱን ይጠብቃል፥ ሕይወትንም የሚወድድ አፉን ይጠብቃል።