ምሳሌ 10:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኃጥእ ወደ ጥፋት ይመለሳል፥ የጻድቅ ምኞቱ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደች ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ ሰው የፈራው ይደርስበታል፤ ጻድቅ የሚመኘው ይፈጸምለታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የክፉ ሰው ፍርሃት በላዩ ይመጣበታል፥ ለጻድቃንም ምኞታቸው ትሰጣቸዋለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደጋግ ሰዎች የሚፈልጉትን ያገኛሉ፤ ክፉዎች ግን እጅግ የፈሩት ነገር ይደርስባቸዋል። |
ጭቅጭቅ ድንገት በመጣባችሁ ጊዜ፥ እንደዚሁም ጥፋታችሁ እንደ ዓውሎ ነፋስ በመጣባችሁ ጊዜ፥ ችግርና ምርኮ በደረሰባችሁ ጊዜ፥ እኔ ከዚያ አለሁ።
እኔ ግን አዋርዳቸው ዘንድ፥ ስለ ኀጢአታቸውም እበቀላቸው ዘንድ እፈቅዳለሁ፤ እኔ በጠራሁ ጊዜ አልመለሱልኝምና፥ በተናገርሁም ጊዜ አልሰሙኝም፤ በፊቴም ክፉ ነገርን አደረጉ፤ ያልወደድሁትንም መረጡ።”