ምሳሌ 1:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ በራሳቸውም ኀጢአት ይጠግባሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፤ የዕቅዳቸውንም ውጤት ይጠግባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ የገዛ ራሳቸውን ምክር ይጠግባሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የሚገባችሁን ቅጣት ትቀበላላችሁ፤ የተንኰላችሁንም ውጤት ታገኛላችሁ። |
ሐሰትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፥ የሥራውንም መቅሠፍት ይፈጽማል። እግዚአብሔር ደስ ብሎት የሚሰጥ ሰውን ይወድዳል፥ ከንቱ ሥራውን ግን ይጠላል።
እኔ ግን አዋርዳቸው ዘንድ፥ ስለ ኀጢአታቸውም እበቀላቸው ዘንድ እፈቅዳለሁ፤ እኔ በጠራሁ ጊዜ አልመለሱልኝምና፥ በተናገርሁም ጊዜ አልሰሙኝም፤ በፊቴም ክፉ ነገርን አደረጉ፤ ያልወደድሁትንም መረጡ።”
ትንቢት የሚናገሩላቸውም ሰዎች ከራብና ከሰይፍ የተነሣ በኢየሩሳሌም መንገዶች ይበተናሉ፤ ክፋታቸውንም አፈስስባቸዋለሁና እነርሱንና ሚስቶቻቸውን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም የሚቀብራቸው አይገኝም።
ክፋትሽ ይገሥጽሻል፤ ክዳትሽም ይዘልፍሻል፤ እኔን መተውሽም ክፉና መራራ ነገር መሆኑን ታውቂያለሽ፤ ትረጂማለሽ” ይላል አምላክሽ እግዚአብሔር፤ “መፈራቴም በአንቺ ዘንድ የለም፤ ይህም ደስ አላሰኘኝም” ይላል አምላክሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እንደ ሥራችሁም ፍሬ እቀጣችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር በዱርዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፤ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።”
ምድር ሆይ፥ ስሚ! እነሆ ቃሌን ስላልሰሙ፥ ሕጌንም ስለ ጣሉ፥ እኔንም ስለ ናቁ በዚህ ሕዝብ ላይ እንደ ሥራቸው ፍሬ፥ ክፉን ነገር አመጣባቸዋለሁ።
ስለዚህ ቍጣዬን አፈሰስሁባቸው፤ በመዓቴም እሳት አጠፋኋቸው፤ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ መለስሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”