ምሳሌ 1:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጠራሁ ጊዜ አልሰማችሁኝምና እጄን ዘረጋሁ፥ ማንም አላስተዋለም ነገርንም አበዛሁ፥ አልመለሳችሁልኝም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን በተጣራሁ ጊዜ እንቢ ስላላችሁኝ፣ እጄንም ስዘረጋ ማንም ግድ ስላልነበረው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጠራሁ ጊዜ እምቢ ስላላችሁ፥ እጄን በዘረጋሁ ጊዜ ማንም ስላላስተዋለ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ እኔ እንድትመጡ እጄን ዘርግቼ ጠራኋችሁ፤ እናንተ ግን ጥሪዬን አልተቀበላችሁም። |
እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወጣ ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ይሳለቁ፥ ቃሉንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።
እነሆ፥ መጣሁ፤ ሰውም አልነበረም፤ ተጣራሁ፤ የሚመልስም አልነበረም፤ እጄ ለማዳን ጠንካራ አይደለምን? ወይስ ለማዳን አልችልምን? እነሆ፥ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም በማጣት ዐሣዎቻቸው ይሞታሉ፤ በጥማትም ያልቃሉ።
እኔም ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ ሁላችሁም በሰይፍ ትገደላላችሁ፤ በፊቴ ክፉ ነገር አደረጋችሁ፤ ያልወደድሁትንም መረጣችሁ እንጂ በጠራኋችሁ ጊዜ አልመለሳችሁልኝምና፥ በተናገርሁም ጊዜ አልሰማችሁኝምና።”
እኔ ግን አዋርዳቸው ዘንድ፥ ስለ ኀጢአታቸውም እበቀላቸው ዘንድ እፈቅዳለሁ፤ እኔ በጠራሁ ጊዜ አልመለሱልኝምና፥ በተናገርሁም ጊዜ አልሰሙኝም፤ በፊቴም ክፉ ነገርን አደረጉ፤ ያልወደድሁትንም መረጡ።”
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በተናገርኋቸው ጊዜ አልሰሙምና፥ በጠራኋቸውም ጊዜ አልመለሱልኝምና የተናገርሁባቸውን ክፉ ነገር ሁሉ በይሁዳ ላይ በኢየሩሳሌምም በሚቀመጡ ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ።”
አሁንም ይህን ነገር ሁሉ ስላደረጋችሁ፥ ተናገርኋችሁ፤ ነገር ግን አልሰማችሁም፤ ጠራኋችሁም፤ ነገር ግን አልመለሳችሁም፤
አራጣንም በአራጣ ላይ ይቀበላሉ፤ ተንኰልን በተንኰል ላይ ይሠራሉ፤ “እኔንም ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፥” ይላል እግዚአብሔር።
ስለዚህ እኔ ደግሞ በመዓት እሠራለሁ፤ ዐይኔ አይራራም፤ እኔም ይቅርታ አላደርግም፤ ወደ ጆሮዬም በታላቅ ድምፅ ቢጮኹ አልሰማቸውም” አለኝ።
በቅዱሱ ልጅህም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሕሙማንን ትፈውስ ዘንድ ተአምራትንና ድንቅ ሥራንም ታደርግ ዘንድ እጅህን ዘርጋ።”
ሳኦልም የእግዚአብሔርን ቃል ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም በሕልም አላሚዎች፥ ወይም በነጋሪዎች፥ ወይም በነቢያት አልመለሰለትም።