ምሳሌ 1:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሕይወት ሳለ እንደ ሲኦል እንዋጠው፥ መታሰቢያውንም ከምድር እናጥፋ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ መቃብር፣ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱ፣ ከነሕይወታቸው በሙሉ እንዋጣቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በሙሉ ሕይወት እያሉ፥ ከነነፍሳቸው፥ እንደ ሲኦል ሆነን እንዋጣቸው፥ ወደ ጉድጓድ እንደሚወድቁም ይሁኑ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቃብር ሙታንን እንደሚውጥ፥ እኛም እነርሱን በሕይወት ሳሉ እንዋጣቸው! ወደ ጒድጓድ እንደሚወርዱም ሰዎች እናድርጋቸው! |
የአማልክት ልጆች ሆይ፥ ለእግዚአብሔር አምጡ፥ የጊደሮችን ጥጃ ለእግዚአብሔር አምጡ። ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ፥
በአፋቸው እውነት የለምና፥ ልባቸውም ከንቱ ነው፥ ጕሮሮኣቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላኝ፤ ከፋፈለኝም፤ እንደ ባዶ ዕቃም አደረገኝ፤ እንደ ዘንዶም ዋጠኝ፤ ከሚጣፍጠውም ሥጋዬ ሆዱን ሞላ።
ዔ። ጠላቶችሽ ሁሉ አፋቸውን አላቀቁብሽ፤ እያፍዋጩና ጥርሳቸውን እያፋጩ፥ “ውጠናታል፤ ነገር ግን ተስፋ ያደረግናት ቀን ይህች ናት፤ አግኝተናታል አይተናትማል” ይላሉ።
ሄ። እግዚአብሔር እንደ ጠላት ሆነብኝ፤ እስራኤልን አሰጠመ። አዳራሾችዋን ሁሉ ዋጠ፤ አንባዎችዋንም አጠፋ። በይሁዳም ሴት ልጅ ውርደትንና ጕስቍልናን አበዛ።
ማኅበሩም በሞቱ ጊዜ ምድሪቱ አፍዋን ከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠቻቸው፤ በዚያም ጊዜ እሳቲቱ ሁለት መቶ አምሳውን ሰዎች አቃጠለቻቸው፤ እነርሱም ለምልክት ሆኑ።