La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ፊልጵስዩስ 3:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱም እንደ ከሃ​ሊ​ነቱ ረዳ​ት​ነት መጠን የተ​ዋ​ረ​ደ​ውን ሥጋ​ች​ንን የሚ​ያ​ድ​ሰው፥ ክቡር ሥጋ​ዉ​ንም እን​ዲ​መ​ስል የሚ​ያ​ደ​ር​ገው፥ የሚ​ያ​ስ​መ​ስ​ለ​ውም፥ ሁሉም የሚ​ገ​ዛ​ለት ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱም ሁሉን ለራሱ ባስገዛበት ኀይል፣ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም ደግሞ ለራሱ ሁሉን ነገር በሥሩ ለማስገዛት በሚችልበት ኃይሉ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርሱ ይህን የተዋረደውን ሰውነታችንን በመለወጥ የእርሱን ክቡር ሰውነት እንዲመስል ያደርገዋል፤ ይህንንም የሚያደርገው ሁሉን በሥልጣኑ ሥር ለማድረግ በሚያስችለው ኀይል ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፥ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።

Ver Capítulo



ፊልጵስዩስ 3:21
18 Referencias Cruzadas  

ባለ ብር ጕብ​ጕብ የሆነ የወ​ርቅ ጠል​ሰም ያድ​ር​ጉ​ልሽ።


ሞት ሰዎ​ችን ዋጠ፤ በረ​ታም፤ እንደ ገናም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊት ሁሉ እን​ባን ያብ​ሳል፤ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ስድብ ከም​ድር ሁሉ ላይ ያስ​ወ​ግ​ዳል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአፉ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


ሙታን ይነ​ሣሉ፤ በመ​ቃ​ብር ያሉም ይድ​ናሉ። በም​ድ​ርም የሚ​ኖሩ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ከአ​ንተ የሚ​ገኝ ጠል መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸው ነውና፤ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ምድር ታጠ​ፋ​ለህ።


ከሲ​ኦል እጅ እታ​ደ​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከሞ​ትም እቤ​ዣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ሞት ሆይ! መው​ጊ​ያህ ወዴት አለ? ሲኦል ሆይ! ድል መን​ሣ​ትህ ወዴት አለ? ደስ​ታህ ከዐ​ይ​ኖ​ችህ ተሰ​ወ​ረች።


በፊታቸውም ተለወጠ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።


ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ።


ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።


ልጁ በብ​ዙ​ዎች ወን​ድ​ሞች መካ​ከል በኵር ይሆን ዘንድ አስ​ቀ​ድሞ ያወ​ቃ​ቸ​ው​ንና የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን እነ​ር​ሱን ልጁን ይመ​ስሉ ዘንድ አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​አ​ቸ​ዋል።


ሕይ​ወ​ታ​ችሁ ክር​ስ​ቶስ በሚ​ገ​ለ​ጥ​በት ጊዜ፥ ያን​ጊዜ ከእ​ርሱ ጋር በፍ​ጹም ክብር ትገ​ለ​ጣ​ላ​ችሁ።


ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።


ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ “አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ፤” ይላል።