እናንተን ለማነጽ እንጂ፥ እናንተን ለማፍረስ ያይደለ፥ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ በሰጠን ሥልጣን እጅግ የተመካሁት መመካት ቢኖር አላፍርም።
ፊልሞና 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ የሚገባውን አዝህ ዘንድ በክርስቶስ ምንም እንኳ ብዙ ድፍረት ቢኖረኝ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ማድረግ የሚገባህን እንድታደርግ አዝዝህ ዘንድ በክርስቶስ ድፍረት ቢኖረኝም፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ የሚገባውን አዝህ ዘንድ በክርስቶስ ምንም እንኳ ብዙ ድፍረት ቢኖረኝ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ተግባርህን ፈጽም ብዬ አንተን ለማዘዝ በክርስቶስ ድፍረት ነበረኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ የሚገባውን አዝህ ዘንድ በክርስቶስ ምንም እንኳ ብዙ ድፍረት ቢኖረኝ፥ |
እናንተን ለማነጽ እንጂ፥ እናንተን ለማፍረስ ያይደለ፥ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ በሰጠን ሥልጣን እጅግ የተመካሁት መመካት ቢኖር አላፍርም።
እኛ እንደ ደካሞች መስለን እንደ ነበርን፥ ይህን በውርደት እናገራለሁ፤ ነገር ግን ማንም በሚደፍርበት እኔ ደግሞ እደፍራለሁ።
የሚያሳፍር ነገርም፥ የስንፍና ነገርም፥ ወይም የማይገባ የዋዛ ነገር በእናንተ ዘንድ አይሁን፤ ማመስገን ይሁን እንጂ።
ነገር ግን እንደምታውቁት በፊልጵስዩስ አስቀድመን መከራ ተቀብለን ተንገላትተንም፥ በብዙ ገድል የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እንናገር ዘንድ በአምላካችን ደፈርን።