እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ።
ዘኍል 8:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይ፤ እነርሱም ለእኔ ይሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ መሠረት ሌዋውያኑን ከእስራኤላውያን ትለያቸዋለህ፤ እነርሱም የእኔ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ትለያለህ፤ ሌዋውያንም ለእኔ ይሆናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ዐይነት ሌዋውያን የኔ ይሆኑ ዘንድ ከቀሩት የእስራኤል ሕዝብ መካከል ለይልኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይ፤ ሌዋውያንም ለእኔ ይሁኑ። |
እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ።
እኔም፦ እነሆ፥ ሌዋውያንን ወንድሞቻችሁን ከእስራኤል ልጆች መካከል ወስጄአለሁ፤ የምስክሩን ድንኳን አገልግሎት ያደርጉ ዘንድ ለእግዚአብሔር የተሰጡ ስጦታዎች ናቸው።
“እነሆ፥ እኔ በእስራኤል ልጆች ዘንድ መጀመሪያ በሚወለደው በበኵር ሁሉ ፋንታ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይች ወስጃለሁ፤ በእነርሱ ፋንታ ሌዋውያን ለእኔ ይሁኑ፤
“ሌዋውያንን በእስራኤል ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ፥ የሌዋውያንንም እንስሶች በእንስሶቻቸው ፋንታ ውሰድ፤ ሌዋውያንም ለእኔ ይሁኑ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝና።
ሌዋውያንንም ወደ ወንድምህ ወደ አሮንና ወደ ልጆቹ ወደ ካህናቱ ታገባቸዋለህ። ከእስራኤል ልጆች ተለይተው ለእኔ ሀብት ሆነው ተሰጥተዋልና።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ወንድ ወይም ሴት ለእግዚአብሔር ራሱን የተለየ ያደርግ ዘንድ ልዩ ስእለት ቢሳል፥
በግብፅ ምድር ያለውን በኵር ሁሉ በገደልሁበት ቀን የእስራኤልን ልጆች በኵራት ሁሉ፥ ሰው ወይም እንስሳ፥ ለእኔ ቀድሼአቸዋለሁና የእኔ ናቸው።
የእግዚአብሔርን ወንጌል ለማስተማር ተለይቶ ከተጠራ ሐዋርያ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ከሚሆን ከጳውሎስ፥
በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ይሸከም ዘንድ፥ እርሱንም ለማገልገል በእግዚአብሔር ፊት ይቆም ዘንድ፥ በስሙም ይባርክ ዘንድ እግዚአብሔር እስከ ዛሬ ድረስ የሌዊን ነገድ ለየ።
ቅዱስና ያለ ተንኰል፥ ነውርም የሌለበት፥ ከኀጢአተኞችም የተለየ፥ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባናል።