ዘኍል 5:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ይመልስለት ዘንድ ሰውዬው ዘመድ ባይኖረው፥ ስለ በደል ለእግዚአብሔር የሚመልሰው ነገር ለካህኑ ይሁን፤ ይህም ስለ እርሱ ማስተስረያ ከሚደረግበት አውራ በግ ላይ ይጨመር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ይህ ሰው ካሳውን የሚቀበልለት ዘመድ ከሌለው ካሳው ለእግዚአብሔር ስለሚሆን ማስተስረያ እንዲሆነው ከሚያቀርበው አውራ በግ ጋራ ለካህኑ ይስጥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በዳዩ ይመልስለት ዘንድ ለተበዳዩ ሰውዮ ዘመድ ባይኖረው፥ ስለ በደል ለጌታ የሚመልሰው ነገር ለካህኑ ይሆናል፥ ይህም ስለ እርሱ ማስተስረያ ከሚደረግበት የማስተስረያ አውራ በግ ላይ ይጨመር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያ ሰው ቢሞትና ካሳውንም የሚቀበልለት የቅርብ ዘመድ ባይኖረው ግን በካህኑ አማካይነት ስጦታው ለእግዚአብሔር ሆኖ ለካህኑ ይሰጥ፤ ይህም ስለ በደል የሚከፈል ዋጋ መሰጠት ያለበት፥ በደል የሠራው ሰው ለኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕትነት ከሚያቀርበው አውራ በግ ጋር ተጨማሪ በመሆን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ይመልስለት ዘንድ ሰውዮው ዘመድ ባይኖረው፥ ስለ በደል ለእግዚአብሔር የሚመልሰው ነገር ለካህኑ ይሁን፥ ይህም ስለ እርሱ ማስተስረያ ከሚደረግበት አውራ በግ በላይ ይጨመር። |
በተቀደሰ ነገር ላይ ስለ ሠራው ኀጢአት ዕዳ ይከፍላል፤ አምስተኛውንም እጅ ይጨምርበታል፤ ለካህኑም ይሰጠዋል። ካህኑም በበደል መሥዋዕት አውራ በግ ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይቅር ይባልለታል።
ወይም በሐሰት የማለበትን ነገር ቢመልስ፥ በሙሉ ይመልስ፤ ከዚያም በላይ አምስተኛውን ክፍል ጨምሮ የበደሉን መሥዋዕት በሚያቀርብበት ቀን ለባለ ገንዘቡ ይስጠው።
የኀጢአት መሥዋዕት እንደ ሆነ እንዲሁ የበደል መሥዋዕት ነው፤ ለሁለቱ አንድ ሕግ ነው፤ በእነርሱ የሚያስተሰርይ ካህን ይወስደዋል።
ያች ሰውነት ብትናዘዝ፥ ያደረገችውንም ኀጢአት ሁሉ ብትናገር የወሰደውን ዓይነቱን ሁሉ ይመልስ። አምስተኛ እጅም ለባለ ገንዘቡ ይጨምር።