ዘኍል 5:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያች ሰውነት ብትናዘዝ፥ ያደረገችውንም ኀጢአት ሁሉ ብትናገር የወሰደውን ዓይነቱን ሁሉ ይመልስ። አምስተኛ እጅም ለባለ ገንዘቡ ይጨምር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሠራው ኀጢአት ይናዘዝ፤ ስለ በደሉም ሙሉ ካሳ ይክፈል፤ የተመደበበትም ካሳ ላይ አንድ ዐምስተኛ በመጨመር በደል ላደረሰበት ሰው ይስጥ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራውንም ኃጢአት ይናዘዝ፤ የወሰደውንም በሙሉ ይመልስ፥ በእርሱም ላይ አምስት እጅ ይጨምርበት፥ ለበደለውም ሰው ይስጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአቱን ይናዘዝ፤ ስለ በደል ሊከፈል በሚገባው ዋጋ ላይ ከመቶ ኻያ እጅ በመጨመር ለተበደለው ሰው ካሳ ይስጥ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወሰደውንም በሙሉ ይመልስ አምስተኛውንም ይጨምርበት፥ ለበደለውም ሰው ይስጠው። |
“እንደ ከዱኝ፥ ቸልም እንዳሉኝ፥ በፊቴም አግድመው እንደ ሄዱ፥ ኀጢአታቸውንና፥ የአባቶቻቸውን ኀጢአት ይናዘዛሉ።
እኔም ደግሞ አግድሜ ከእነርሱ ጋር በቍጣ ሄድሁ፤ በጠላቶቻቸውም ምድር አጠፋቸዋለሁ። ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ያፍራል፤ ስለ ኀጢአታቸውም ይናዘዛሉ፤
“ሰው ቢዘነጋ፥ ሳያውቅም ለእግዚአብሔር በተቀደሰው በማናቸውም ነገር ኀጢአትን ቢሠራ፥ ለበደል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ከመንጋዉ ነውር የሌለበትን እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን በብር ሰቅል የተገመተውን አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት ያቀርባል።
በተቀደሰ ነገር ላይ ስለ ሠራው ኀጢአት ዕዳ ይከፍላል፤ አምስተኛውንም እጅ ይጨምርበታል፤ ለካህኑም ይሰጠዋል። ካህኑም በበደል መሥዋዕት አውራ በግ ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይቅር ይባልለታል።
የኀጢአት መሥዋዕት እንደ ሆነ እንዲሁ የበደል መሥዋዕት ነው፤ ለሁለቱ አንድ ሕግ ነው፤ በእነርሱ የሚያስተሰርይ ካህን ይወስደዋል።
ነገር ግን ይመልስለት ዘንድ ሰውዬው ዘመድ ባይኖረው፥ ስለ በደል ለእግዚአብሔር የሚመልሰው ነገር ለካህኑ ይሁን፤ ይህም ስለ እርሱ ማስተስረያ ከሚደረግበት አውራ በግ ላይ ይጨመር።
ዘኬዎስም ቆመና ጌታችንን እንዲህ አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አሁን የገንዘቤን እኩሌታ ለነዳያን እሰጣለሁ፤ የበደልሁትም ቢኖር ስለ አንድ ፋንታ አራት እጥፍ እከፍለዋለሁ።”
ኢያሱም አካንን፥ “ልጄ ሆይ! ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ፤ ለእርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ አትሸሽገኝም” አለው።