ዘኍል 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ሴቲቱን በመርገም መሐላ ያምላታል፤ ካህኑም ሴቲቱን እንዲህ ይበላት፦ እግዚአብሔር የተረገምሽ ያድርግሽ ጎንሽን ያረግፈው ዘንድ እግዚአብሔር ከሕዝብሽ መካከል ለይቶ ያጥፋሽ፤ ሆድሽን ይሰንጥቀው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እዚህ ላይ ካህኑ እንዲህ በማለት ሴትዮዋን በርግማን መሐላ ያስምላታል፤ “እግዚአብሔር ጭንሽን እያሰለለና ሆድሽን እያሳበጠ በሕዝብሽ መካከል ርግማንና መሐላ ያድርግብሽ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም ሴቲቱን በመርገም መሐላ ያምላታል፥ ካህኑም ሴቲቱን እንዲህ ይላታል፦ ‘ጌታ ጭንሽን እያመነመነ ሆድሽንም እየነፋ፥ በሕዝብሽ መካከል ጌታ ለመርገምና ለመሐላ የምትሆኚ ያድርግሽ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑ ሴቲቱን እንዲህ ብሎ የመርገም መሐላ ያስሞላት፦ ‘እግዚአብሔር ጭንሽን እያሰለሰለና ሆድሽን እየነፋ በሕዝብሽ መካከል ለመሓላና ለእርግማን የተገባሽ ያድርግሽ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ሴቲቱን በመርገም መሐላ ያምላታል፥ ካህኑም ሴቲቱን፦ እግዚአብሔር ጭንሽን እያሰለሰለ ሆድሽንም እየነፋ፥ እግዚአብሔር ለመርገምና ለመሐላ በሕዝብሽ መካከል ያድርግሽ፤ |
በእግዚአብሔርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተሰጠው በእግዚአብሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ፥ ፍርዱንም፥ ሥርዐቱንም ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ ርግማንንና መሐላን አደረጉ።
ስማችሁንም እኔ ለመረጥኋቸው ሕዝቤ ጥጋብ አድርጋችሁ ትተዋላችሁ፤ ጌታ እግዚአብሔርም ያጠፋችኋል፤ ባሪያዎች ግን በሐዲስ ስም ይጠራሉ።
ከእነርሱም የተነሣ በባቢሎን ያሉ የይሁዳ ምርኮኞች ሁሉ፦ የባቢሎን ንጉሥ በእሳት እንደ ጠበሳቸው እንደ ሴዴቅያስና እንደ አክዓብ እግዚአብሔር ያድርግህ የምትባል ርግማንን ያነሣሉ፤
ውኃውን ካጠጣት በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ ራስዋን አርክሳና ባልዋን ቸል ብላው ከሆነ፤ የመርገሙ መራራ ውኃ ወደ ሆድዋ ይገባል፤ ሆድዋንም ይሰነጥቀዋል፤ ጎኗም ይረግፋል፤ ሴቲቱም በሕዝብዋ መካከል ለመርገም ትሆናለች።
በዚያችም ቀን ኢያሱ፥ “ይህችን ከተማ ኢያሪኮን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ርጉም ይሁን፤ መሠረቷን በበኵር ልጁ የሚጥል፥ በሮችዋንም በታናሹ ልጁ የሚያቆም ርጉም ይሁን” ብሎ ማለ።
ሳኦልም በዚያ ቀን ትልቅ በደል ፈጸመ፤ “ጠላቶቼን እስክበቀል እስከ ማታ ድረስ መብል የሚበላ ሰው ርጉም ይሁን” ብሎ ሕዝቡን አምሎአቸው ነበርና። ሕዝቡም ሁሉ እህል አልቀመሱም። ሀገሩም ሁሉ ምሳ አልበላም።