ዘኍል 5:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ሴቲቱን በእግዚአብሔር ፊት ያቆማታል፤ የሴቲቱንም ራስ ይገልጣል፤ በእጅዋም ለመታሰቢያ የሚሆነውን የእህል ቍርባን፥ የቅንዐት ቍርባን ያኖራል፤ በካህኑም እጅ ርግማንን የሚያመጣው መራራ ውኃ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑ ሴትዮዋን በእግዚአብሔር ፊት እንድትቆም ካደረገ በኋላ የጠጕሯን መሸፈኛ ይገልጣል፤ ስለ ቅናት የቀረበውን የመታሰቢያ ቍርባን በእጇ ያስይዛታል፤ ከዚያም ካህኑ ርግማን የሚያመጣውን መራራ ውሃ በእጁ ይይዛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም ሴቲቱን በጌታ ፊት ያቆማታል፥ የሴቲቱንም የተሠራ ጠጉር ይፈታል፥ በእጅዋም የመታሰቢያ የእህል ቁርባን የሆነውን የቅንዓት የእህል ቁርባን ያኖራል፤ ካህኑም እርግማንን የሚያመጣውን መራራ ውኃ በእጁ ይይዛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም ሴትዮዋን በእግዚአብሔር ፊት ያቁማት፤ የራስዋንም ጠጒር ይፍታ፤ የቅናቱንም የእህል ቊርባን በእጅዋ ላይ ያስቀምጥ፤ በእጁም እርግማንን የሚያመጣ መራራ ውሃ ይያዝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ሴቲቱን በእግዚአብሔር ፊት ያቆማታል፥ የሴቲቱንም ራስ ይገልጣል፥ በእጅዋም ለመታሰቢያ የሚሆነውን የእህል ቍርባን፥ ለቅንዓት ቍርባን፥ ያኖራል፤ በካህኑም እጅ እርግማንን የሚያመጣው መራራ ውኃ ይሆናል። |
እኔም ከሞት ይልቅ የመረረች ነገርን አገኘሁ፤ እርስዋም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ በእጆችዋም ማሰሪያ ያላት ሴት ናት፤ በእግዚአብሔርም ፊት ደግ የሆነ ከእርሷ ያመልጣል። ኀጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።
ክፋትሽ ይገሥጽሻል፤ ክዳትሽም ይዘልፍሻል፤ እኔን መተውሽም ክፉና መራራ ነገር መሆኑን ታውቂያለሽ፤ ትረጂማለሽ” ይላል አምላክሽ እግዚአብሔር፤ “መፈራቴም በአንቺ ዘንድ የለም፤ ይህም ደስ አላሰኘኝም” ይላል አምላክሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ያ ሰው ሚስቱን ወደ ካህኑ ያምጣት፤ የኢፍ መስፈሪያም ዐሥረኛ እጅ ገብስ ዱቄት ቍርባን ስለ እርስዋ ያምጣ፤ የቅንዐት ቍርባን ነውና፥ ኀጢአትንም የሚያሳስብ የመታሰቢያ ቍርባን ነውና ዘይት አያፍስስበት፤ ዕጣንም አይጨምርበት።
ካህኑም የተቀደሰ ውኃ በሸክላ ማሰሮ ይወስዳል፤ ካህኑም በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ካለው ትቢያ ወስዶ በውኃ ላይ ይረጨዋል፤
ካህኑም ያምላታል፤ ሴቲቱንም እንዲህ ይላታል፦ ሌላ ወንድ አልተኛሽ፥ ባልሽንም አልተውሽ፥ ራስሽንም አላረከስሽ እንደ ሆነ፥ ርግማንን ከሚያመጣ ከዚህ መራራ ውኃ ንጹሕ ሁኚ፤
ርግማንንም የሚያመጣ ይህ ውኃ ወደ ሆድሽ ይግባ፥ ማኅፀንሽንም ይሰንጥቀው፤ ጎንሽም ይርገፍ። ሴቲቱም፦ ይሁን ይሁን ትላለች።
ሄዶ የእነዚያን አሕዛብ አማልክት ያመልክ ዘንድ ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ልቡን ዛሬ የሚያስት ወንድ ወይም ሴት ወይም ወገን ወይም ነገድ አይኑርባችሁ፤ ሐሞትና እሬትም የሚያበቅል ሥር አይሁንባችሁ።
መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፥ ለመኝታቸውም ርኵሰት የለውም፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።
ሳሙኤልም፥ “የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ” አለ። አጋግም እየተንቀጠቀጠ ወደ እርሱ መጣ። አጋግም፥ “በውኑ ሞት እንደዚህ መራራ ነውን?” አለ።