ዘኍል 4:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ እያንዳንዳቸው በየአገልግሎታቸውና በየሸክማቸው በሙሴ እጅ ተቈጠሩ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ በእርሱ ተቈጠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እያንዳንዱ በየአገልግሎቱና በየሸክም ሥራው ተደለደለ። ስለዚህም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ቈጠራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ጌታ ትእዛዝ እያንዳንዳቸው በየአገልግሎታቸውና በየሸክማቸው በሙሴ ተደለደሉ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ በእርሱ ተቈጠሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ዐይነት እያንዳንዱ ሰው እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ተቈጠረ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እያንዳንዱ የማገልገልንና የመሸከምን ኀላፊነት ተቀበለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ እያንዳንዳቸው በየአገልግሎታቸውና በየሸክማቸው በሙሴ እጅ ተቈጠሩ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ በእርሱ ተቈጠሩ። |
አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና የመቅደሱን ዕቃ ሁሉ ሸፍነው ከጨረሱ በኋላ ሰፈሩ ሲነሣ የቀዓት ልጆች ሊሸከሙት ይገባሉ። እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን አይንኩ። በምስክሩ ድንኳን ዘንድ የቀዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው።
በምስክሩ ድንኳን ዘንድ ባለው አገልግሎታቸው ሁሉ፥ የድንኳኑ ሳንቆች፥ መወርወሪያዎቹም፥ ተራዳዎቹም፥ እግሮቹም፥ መሸፈኛዎቹም፥ መቀመጫዎቹም፥ የምስክሩ ድንኳን ደጃፍ መጋረጃ፥
በዙሪያውም የሚቆሙት የአደባባዩ ምሰሶዎች፥ እግሮቹም፥ የአደባባዩ ደጃፍ መጋረጃ ምሰሶዎች፥ እግሮቻቸውም፥ ካስማዎቹም፥ አውታሮቹም፥ ዕቃዎቹና ማገልገያዎቹ ሸክማቸው ነው፤ የሚጠብቁትንም የሸክማቸውን ዕቃ ሁሉ በየስማቸው ቍጠሩ።
እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ፥ ሙሴና አሮን እንደ ቈጠሩአቸው በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ያገለግሉ ዘንድ የሚገቡት ሁሉ፥ የቀዓት ልጆች ቍጥር ይህ ነው።
እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ፥ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ያገለገሉት ሁሉ የጌድሶን ልጆች ቍጥር ይህ ነው።