Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 4:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የጌ​ድ​ሶን ወገ​ኖች ሥራ በማ​ገ​ል​ገ​ልና በመ​ሸ​ከም ይህ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 “የጌርሶናውያን ወገኖች የሥራና የሸክም አገልግሎታቸው ይህ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 የጌድሶናውያን ወገኖች በማገልገልና በመሸከም የሚሰጡት አገልግሎት ይህ ነው፦

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እነርሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን የመሸከም ኀላፊነት ይኖራቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 የጌድሶናውያን ወገኖች ሥራ በማገልገልና በመሸከም ይህ ነው፤

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 4:24
12 Referencias Cruzadas  

እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውና በየ​ሸ​ክ​ማ​ቸው በሙሴ እጅ ተቈ​ጠሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ እን​ዲሁ በእ​ርሱ ተቈ​ጠሩ።


በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ሥራ​ውን ለመ​ሥ​ራ​ትና ዕቃ​ውን ለመ​ሸ​ከም የገ​ቡት ሁሉ፥ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉት፥


የጌ​ድ​ሶን ልጆች አገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ፥ በተ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ፥ በሥ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ በአ​ሮ​ንና በል​ጆቹ ትእ​ዛዝ ይሁን፤ በስ​ማ​ቸ​ውና በተ​ራ​ቸ​ውም ትቈ​ጥ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።


ነገር ግን ወደ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ በቀ​ረቡ ጊዜ በሕ​ይ​ወት ይኖሩ ዘንድ እንጂ እን​ዳ​ይ​ሞቱ እን​ዲሁ አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ አሮ​ንና ልጆቹ ይግቡ፤


አሮ​ንና ልጆቹ መቅ​ደ​ሱ​ንና የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ ሁሉ ሸፍ​ነው ከጨ​ረሱ በኋላ ሰፈሩ ሲነሣ የቀ​ዓት ልጆች ሊሸ​ከ​ሙት ይገ​ባሉ። እን​ዳ​ይ​ሞቱ ግን ንዋየ ቅድ​ሳ​ቱን አይ​ንኩ። በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ የቀ​ዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው።


የጌ​ድ​ሶን ልጆች በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን የሚ​ጠ​ብ​ቁት ማደ​ሪ​ያ​ውና ድን​ኳኑ፥ መደ​ረ​ቢ​ያ​ውም፥ የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ መጋ​ረጃ፥


የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​ትን ሁሉ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠ​ራ​ቸው።


የድ​ን​ኳ​ኑን መጋ​ረ​ጃ​ዎች፥ የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን፥ መደ​ረ​ቢ​ያ​ውን፥ በላ​ዩም ያለ​ውን የአ​ቆ​ስ​ጣ​ውን ቍር​በት መደ​ረ​ቢያ፥ የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን ደጃፍ መጋ​ረጃ፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም መጋ​ረጃ፥


ለጌ​ድ​ሶን ልጆች እንደ አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ሁለት ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና አራት በሬ​ዎ​ችን ሰጣ​ቸው።


የአ​ደ​ባ​ባዩ መጋ​ረጃ፥ በድ​ን​ኳኑ አደ​ባ​ባይ በር ያለው መጋ​ረ​ጃና የቀ​ረ​ውም ሥራዋ ሁሉ ይሆ​ናል።


ድን​ኳ​ኑም ተነ​ቀለ፤ ድን​ኳ​ኑ​ንም የተ​ሸ​ከሙ የጌ​ድ​ሶን ልጆ​ችና የሜ​ራሪ ልጆች ተጓዙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios