Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 4:49 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

49 በዚህም ዐይነት እያንዳንዱ ሰው እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ተቈጠረ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እያንዳንዱ የማገልገልንና የመሸከምን ኀላፊነት ተቀበለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

49 እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እያንዳንዱ በየአገልግሎቱና በየሸክም ሥራው ተደለደለ። ስለዚህም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ቈጠራቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

49 እንደ ጌታ ትእዛዝ እያንዳንዳቸው በየአገልግሎታቸውና በየሸክማቸው በሙሴ ተደለደሉ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ በእርሱ ተቈጠሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

49 እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውና በየ​ሸ​ክ​ማ​ቸው በሙሴ እጅ ተቈ​ጠሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ እን​ዲሁ በእ​ርሱ ተቈ​ጠሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

49 እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ እያንዳንዳቸው በየአገልግሎታቸውና በየሸክማቸው በሙሴ እጅ ተቈጠሩ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ በእርሱ ተቈጠሩ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 4:49
18 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሁሉን ነገር አደረጉ።


እነርሱ መሸከም ያለባቸው ተራዳዎችን፥ መወርወሪያዎችን፥ ምሰሶችን፥ የማደሪያው ድንኳን የሚቆምባቸውን እግሮች፥


እነርሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን የመሸከም ኀላፊነት ይኖራቸዋል።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤


ከሰፈር በሚነሡበትም ጊዜ አሮንና ልጆቹ ንዋያተ ቅድሳቱንና የእነርሱንም መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ከሸፈኑ በኋላ የቀዓት ልጆች መጥተው ይሸከሙአቸው፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ ንዋያተ ቅድሳቱን መንካት አይገባቸውም፤ እንግዲህ የመገናኛው ድንኳን በሚነሣበት ጊዜ ሁሉ የቀዓት ልጆች ኀላፊነት ይህ ነው።


እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በመገናኛው ድንኳን ያገለገሉትና ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው የሜራሪ ልጆች እነዚህ ናቸው።


እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በመገናኛው ድንኳን ያገለገሉትና ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው የጌርሾን ልጆች እነዚህ ናቸው።


እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በመገናኛው ድንኳን ያገለገሉትና ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው የቀዓት ቤተሰቦች ሁሉ እነዚህ ነበሩ።


እግዚአብሔር ባዘዘው ቃል መሠረት ሙሴ የመዋጃውን ገንዘብ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጠ።


ሌዋውያን ግን እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት፥ ከሌሎቹ የእስራኤል ሕዝብ ጋር አልተቈጠሩም።


ሌዋውያን ግን ከሌሎች ነገዶች ጋር አብረው አልተቈጠሩም።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤


እንዲሁም በድንኳኑ ዙሪያ የሚገኘውን አደባባይ ምሰሶችን፥ እግሮቻቸውን፥ ካስማዎችን፥ አውታሮችንና ለእነዚህ ሁሉ መገልገያ የሆኑትን ዕቃዎች ነው፤ እያንዳንዱም መሸከም ያለበትን ዕቃ በየስሙ ትመድብለታለህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios