La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 4:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በመ​ቅ​ደ​ስም ውስጥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ትን የማ​ገ​ል​ገ​ያ​ውን ዕቃ ሁሉ ይው​ሰዱ፤ በሰ​ማ​ያ​ዊ​ዉም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ውስጥ ያስ​ቀ​ም​ጡት፤ በአ​ቆ​ስ​ጣም ቍር​በት መሸ​ፈኛ ይሸ​ፍ​ኑት፤ በመ​ሸ​ከ​ሚ​ያ​ውም ላይ ያድ​ር​ጉት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“እንዲሁም በመቅደሱ ውስጥ ለአገልግሎት የሚሆኑትን ዕቃዎች በሙሉ ወስደው በሰማያዊ ጨርቅ በአቆስጣ ቍርበት በመሸፈን በመሸከሚያው ሳንቃ ላይ ያስቀምጡት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በመቅደስም ውስጥ የሚገለገሉባቸውን የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ይውሰዱ፥ በሰማያዊውም መጐናጸፊያ ውስጥ ያስቀምጡአቸው፥ በአቆስጣም ቁርበት መሸፈኛ ይሸፍኑአቸው፥ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉአቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በመቅደሱ መገልገያ የሆኑትን ዕቃዎች ሁሉ ወስደው በሰማያዊ ጨርቅ ይሸፍኑአቸው፤ የለፋ ስስ ቊርበት ደርበውም በመሸከሚያው ተራዳ ላይ ያኑሩአቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በመቅደስም ውስጥ የሚያገልግሉበትን የማገልገያውን ዕቃ ሁሉ ይውሰዱ፥ በሰማያዊውም መጐናጸፊያ ውስጥ ያስቀምጡት፥ በአቆስጣም ቁርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት፥ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉት።

Ver Capítulo



ዘኍል 4:12
16 Referencias Cruzadas  

ዕቃ​ው​ንም በቍ​ጥር ያገ​ቡና ያወጡ ነበ​ርና ከእ​ነ​ዚህ አን​ዳ​ን​ዶቹ በማ​ገ​ል​ገ​ያው ዕቃ ላይ ሹሞች ነበሩ።


ከእ​ነ​ርሱ አን​ዳ​ን​ዶቹ በአ​ገ​ል​ግ​ሎቱ ዕቃ​ዎች በመ​ቅ​ደሱ ዕቃ ሁሉ፥ በመ​ል​ካ​ሙም ዱቄት፥ በወ​ይን ጠጁም፥ በዘ​ይ​ቱም፥ በዕ​ጣ​ኑም፥ በሽ​ቱ​ውም ላይ ሹሞች ነበሩ።


ኪራ​ምም ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንና መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹን፥ በመ​ሠ​ዊ​ያው ቤት ያሉ ማን​ኪ​ያ​ዎ​ች​ንና የመ​ገ​ል​ገ​ያ​ውን ዕቃ ሁሉ ሠራ። ኪራ​ምም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ።


የእ​ግር መታ​ጠ​ቢ​ያ​ዎ​ችን፥ የእጅ መታ​ጠ​ቢ​ያ​ዎ​ችን፥ ጋኖ​ችን፥ የሥጋ ማውጫ ሜን​ጦ​ዎ​ች​ንና ኪራም የሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ ከን​ጹሕ ናስ ሠርቶ ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አቀ​ረ​በ​ለት።


ሰሎ​ሞ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የነ​በ​ረ​ውን ዕቃ ሁሉ፥ የወ​ር​ቁ​ንም መሠ​ዊያ፥ ኅብ​ስተ ገጽ የነ​በ​ረ​ባ​ቸ​ውን ገበ​ታ​ዎች ሠራ።


ውስ​ጠ​ኛው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ደጅና ወደ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ መግ​ቢያ የሚ​ወ​ስ​ደው የው​ስ​ጠ​ኛ​ውም የቤተ መቅ​ደሱ ደጆች የወ​ርቅ ነበሩ። እን​ዲ​ሁም ሰሎ​ሞን ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሠ​ራው ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ።


የፍ​የ​ልም ጠጕር፥ ቀይ የተ​ለፋ የአ​ውራ በግ ቍር​በት፥ ሰማ​ያዊ ቀለም የገባ ቍር​በት፥ የማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት፥


በተ​ራ​ራው እን​ዳ​ሳ​የ​ሁህ ሁሉ፥ እንደ ማደ​ሪ​ያው ምሳሌ፥ እንደ ዕቃ​ውም ሁሉ ምሳሌ ለእኔ ትሠ​ራ​ለህ፤ እን​ዲሁ ትሠ​ራ​ለህ።


በክ​ህ​ነት እኔን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ትን የካ​ህ​ኑን የአ​ሮ​ንን ልብሰ ተክ​ህ​ኖና የል​ጆ​ቹን ልብስ፥


እንደ ድን​ኳኑ ሥራ​ዎች ሁሉ የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ዕቃና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሕግ ይጠ​ብቁ።


በወ​ር​ቁም መሠ​ዊያ ላይ ሰማ​ያ​ዊ​ውን መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይዘ​ር​ጉ​በት፤ በአ​ቆ​ስ​ጣም ቍር​በት መሸ​ፈኛ ይሸ​ፍ​ኑት፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያግቡ።


አመ​ዱ​ንም ያስ​ወ​ግዱ፤ መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያድ​ርጉ፤ ሐም​ራ​ዊ​ዉ​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይዘ​ር​ጉ​በት፤


በላ​ዩም የአ​ቆ​ስ​ጣ​ውን ቍር​በት መሸ​ፈኛ ያድ​ር​ጉ​በት፤ ከእ​ር​ሱም በላይ ሁለ​ን​ተ​ናው ሰማ​ያዊ የሆነ መጐ​ና​ጸ​ፊያ ያግ​ቡ​በት፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያግ​ቡ​በት።


በኅ​ብ​ስተ ገጹ ገበታ ላይም ሰማ​ያ​ዊ​ውን መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይዘ​ር​ጉ​በት፤ በእ​ር​ሱም ላይ ወጭ​ቶ​ቹን፥ ጭል​ፋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ጽዋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ለማ​ፍ​ሰ​ስም መቅ​ጃ​ዎ​ቹን ያድ​ር​ጉ​በት፤ ሁል​ጊ​ዜም የሚ​ኖር ኅብ​ስት በእ​ርሱ ላይ ይሁን።


ሰማ​ያ​ዊ​ው​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይው​ሰዱ፤ የሚ​ያ​በ​ሩ​ባ​ት​ንም መቅ​ረዝ፥ ቀን​ዲ​ሎ​ች​ዋ​ንም፥ መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ የኵ​ስ​ታሪ ማድ​ረ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ እር​ስ​ዋ​ንም ለማ​ገ​ል​ገል የዘ​ይ​ቱን ማሰ​ሮ​ዎች ሁሉ ይሸ​ፍኑ፤