የተወደደችውን የእግዚአብሔርንም ዓመት የተመረጠች ብዬ እጠራት ዘንድ፥ አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፥
ዘኍል 36:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእስራኤልም ልጆች ኢዮቤልዩ በሆነ ጊዜ ርስታቸው ሴቶቹ ወደ አገቡበት ወደ ሌላ ነገድ ርስት ይጨመራል፤ እነሆ፥ ርስታቸው ከአባቶቻችን ነገድ ርስት ይጐድላል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤላውያን ዓመተ ኢዮቤልዩ በሚመጣበት ጊዜ የእነርሱ ድርሻ ወደ ባሎቻቸው ነገድ ይጨመራል፤ ይህ ከሆነም ድርሻቸው ከአባቶቻችን ነገድ ርስት ላይ ይወሰዳል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእስራኤልም ልጆች ኢዮቤልዩ በመጣ ጊዜ ርስታቸው እነርሱ ወደ አሉበት ነገድ ርስት ይጨመራል፤ ርስታቸውም ከአባቶቻችን ነገድ ርስት ይወሰዳል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንብረት በሚመለስበት ዓመት የተሸጠ ንብረት ሁሉ ለባለቤቱ በሚመለስበት ጊዜ የጸሎፍሐድ ሴቶች ልጆች ርስት አግብተው ወደ ሄዱበት ነገድ ለዘለቄታው ተጨማሪ ሆኖ ይተላለፋል፤ ይህም በእኛ ነገድ ይዞታ ላይ ጒድለትን ያስከትላል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእስራኤልም ልጆች ኢዮቤልዩ በመጣ ጊዜ ርስታቸው ለሚሆኑበት ነገድ ርስት ይጨመራል፤ እነዚህም ርስታቸው ከአባቶቻችን ነገድ ርስት የጐድላል። |
የተወደደችውን የእግዚአብሔርንም ዓመት የተመረጠች ብዬ እጠራት ዘንድ፥ አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፥
“የዓመታትን ሰባት ሰንበቶች ሰባት ጊዜ ሰባት ለራስህ ትቈጥራለህ፤ እነዚህም ሰባት የዓመታት ሱባዔያት አርባ ዘጠኝ ዓመታት ይሆናሉ።
ከሌላም ከእስራኤል ልጆች ነገድ ባል ቢያገቡ፥ ርስታቸው ከአባቶቻችን ርስት ይነቀላል፤ እነርሱም ለሚገቡበት ለሌላው ነገድ ርስት ይጨመራል፤ እንደዚህም የርስታችን ዕጣ ይጐድላል።