ዘኍል 36:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ከሌላም ከእስራኤል ልጆች ነገድ ባል ቢያገቡ፥ ርስታቸው ከአባቶቻችን ርስት ይነቀላል፤ እነርሱም ለሚገቡበት ለሌላው ነገድ ርስት ይጨመራል፤ እንደዚህም የርስታችን ዕጣ ይጐድላል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ከሌሎች የእስራኤል ነገዶች ባል ቢያገቡ ድርሻቸው ከእኛ የዘር ርስት ላይ ተወስዶ የሚያገቧቸው ሰዎች ላሉበት ነገድ ይተላለፋል፤ ይህ ከሆነ ደግሞ በዕጣ ከተደለደለልን ርስት ላይ ከፊሉ ሊቀነስብን ነው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ከሌላም ከእስራኤል ልጆች ነገድ ባል ቢያገቡ፥ ርስታቸው ከአባቶቻችን ርስት ይወሰዳል፥ እነርሱም ወደ አሉበት ወደ ለሌላው ነገድ ርስት ይጨመራል፤ እንደዚህም ከርስታችን ዕጣ ይወሰዳል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ነገር ግን እነርሱ ከሌላ ነገድ የሆኑ ወንዶችን ቢያገቡ ርስታቸው የዚያ ነገድ መሆን እንደሚገባውና የእኛም ድርሻ ሊቀነስ እንደሚችል አስታውስ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ከሌላም ከእስራኤል ልጆች ነገድ ባል ቢያገቡ፥ ርስታቸው ከአባቶቻችን ርስት ይነቀላል፥ እነርሱም ለሚሆኑበት ለሌላው ነገድ ርስት ይጨመራል፤ እንደዚህም የርስታችን ዕጣ ይጐድላል። Ver Capítulo |