La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 35:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ታላቁ ካህን እስ​ኪ​ሞት ወደ ምድሩ ትመ​ል​ሱት ዘንድ ወደ መማ​ፀ​ኛው ከተማ ከሸ​ሸው ዋጋ አት​ቀ​በሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘ወደ መማጸኛ ከተማ ሸሽቶ ስለ ገባ ስለ ማንኛውም ሰው የደም ዋጋ በመቀበል ሊቀ ካህናቱ ከመሞቱ በፊት ወደ አገሩ ተመልሶ ሄዶ እዚያ እንዲኖር አታድርጉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ታላቁ ካህን ሳይሞት ወደ ምድሩ እንዲመለስ ወደ መማፀኛው ከተማ ከሸሸው ሰው የነፍስ ዋጋ አትቀበሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንድ ሰው ወደ መማጸኛ ከተማ ሸሽቶ ቢያመልጥ ሊቀ ካህናቱ ከመሞቱ በፊት ወደ ቤቱ መመለስ ይችል ዘንድ ገንዘብ እንዲከፍል አትፍቀዱለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዋነኛው ካህን ሳይሞት ወደ ምድሩ ይመለስ ዘንድ ወደ መማፀኛው ከተማ ከሸሸው የነፍስ ዋጋ አትቀበሉ።

Ver Capítulo



ዘኍል 35:32
8 Referencias Cruzadas  

የገ​ባ​ዖን ሰዎ​ችም፥ “ከሳ​ኦ​ልና ከቤቱ ወርቅ ወይም ብር አን​ፈ​ል​ግም፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወገን እኛ የም​ን​ገ​ድ​ለው የለም” አሉት።


ሞት የተ​ፈ​ረ​ደ​በ​ትን ነፍሰ ገዳ​ዩ​ንም ለማ​ዳን የነ​ፍስ ዋጋ አት​ቀ​በሉ፤ እርሱ ፈጽሞ ይገ​ደል።


ምድ​ርን የሚ​ያ​ረ​ክ​ሳት ደም ነውና የም​ት​ኖ​ሩ​ባ​ትን ምድር በነ​ፍስ ግድያ አታ​ር​ክ​ሷት። ምድ​ሪ​ቱም በደም አፍ​ሳሹ ደም ካል​ሆነ በቀር ከፈ​ሰ​ሰ​ባት ደም አት​ነ​ጻም።


መዳ​ንም በሌላ በማ​ንም የለም፤ ከሰ​ማይ በታች እን​ድ​ን​በት ዘንድ የሚ​ገ​ባን ለሰው የተ​ሰጠ ሌላ ስም ከቶ የለ​ምና።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ጸጋ አል​ክ​ድም፤ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት የሚ​ጸ​ድቁ ከሆነ እን​ኪ​ያስ ክር​ስ​ቶስ በከ​ንቱ ሞተ።


ነገር ግን ተስፋ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በማ​መን ይሆን ዘንድ፥ ያመ​ኑ​ትም ያገ​ኙት ዘንድ፥ መጽ​ሐፍ ሁሉን በኀ​ጢ​አት ዘግ​ቶ​ታል።


“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።