ዘኍል 35:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)33 ምድርን የሚያረክሳት ደም ነውና የምትኖሩባትን ምድር በነፍስ ግድያ አታርክሷት። ምድሪቱም በደም አፍሳሹ ደም ካልሆነ በቀር ከፈሰሰባት ደም አትነጻም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም33 “ ‘ደም ምድሪቱን ስለሚያረክሳት፣ ደም ለፈሰሰባትም ምድር ስርየት ሊደረግላት የሚችለው በሌላ ሳይሆን በዚያው ደሙን ባፈሰሰው ሰው ደም ብቻ በመሆኑ፣ የምትኖሩባትን ምድር በደም አታርከሷት፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)33 ደም ምድሪቱን ያረክሳታልና የምትኖሩባትን ምድር አታርክሱአት፤ በደም አፍሳሹ ደም ካልሆነ በቀር ምድሪቱ ከፈሰሰባት ደም አትነጻም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም33 ይህን ብታደርጉ የምትኖሩበትን ምድር ታረክሳላችሁ፤ የነፍስ ግድያ ወንጀል ምድሪቱን ያረክሳል፤ ስለዚህ የነፍሰ ገዳዩ ደም ካልፈሰሰ በቀር ምድሪቱን ከደም ለማንጻት የሚፈጸም ሌላ ሥርዓት የለም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)33 ደም ምድሪቱን ያረክሳታልና የምትኖሩባትን ምድር አታርክሱአት፤ በደም አፍሳሹ ደም ካልሆነ በቀር ምድሪቱ ከፈሰሰባት ደም አትነጻም። Ver Capítulo |