ዳዊትም የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ፥ “መልካም መስሎ የታያችሁ እንደ ሆነ፥ አምላካችን እግዚአብሔርም ፈቅዶ እንደ ሆነ፥ በእስራኤል ሀገር ሁሉ ለቀሩት ወንድሞቻችን በከተሞቻቸውና በመሰማሪያዎቻቸው ለሚቀመጡ ካህናትና ሌዋውያን ወደ እኛ ይሰበሰቡ ዘንድ እንላክ።
ዘኍል 35:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሌዋውያን የሚቀመጡባቸውን ከተሞች ከሚካፈሉት ርስታቸው ይሰጡ ዘንድ የእስራኤልን ልጆች እዘዛቸው፤ በከተሞቹም ዙሪያ ያሉትን መሰማሪያዎች ለሌዋውያን ይስጡአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከሚወርሱት ርስት ላይ ለሌዋውያን የሚኖሩባቸውን ከተሞች እንዲሰጧቸው እስራኤላውያንን እዘዛቸው፤ በየከተሞቹ ዙሪያም የግጦሽ መሬት ሰጧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሌዋውያን የሚቀመጡባቸውን ከተሞች ከርስታቸው እንዲሰጡ የእስራኤልን ልጆች እዘዛቸው፤ በከተሞቹም ዙሪያ ያለውን መሰማሪያ ለሌዋውያን ስጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስራኤላውያን ድርሻቸው ከሆነ ርስት ለሌዋውያን የሚኖሩባቸውን ከተሞችንና በከተሞቹም ዙሪያ የግጦሽ መሬት እንዲሰጡአቸው ንገር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌዋውያን የሚቀመጡባቸውን ከተሞች ከርስታቸው ይሰጡ ዘንድ የእስራኤልን ልጆች እዘዛቸው፤ በከተሞቹም ዙሪያ ያለውን መሰምርያ ለሌዋውያን ስጡ። |
ዳዊትም የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ፥ “መልካም መስሎ የታያችሁ እንደ ሆነ፥ አምላካችን እግዚአብሔርም ፈቅዶ እንደ ሆነ፥ በእስራኤል ሀገር ሁሉ ለቀሩት ወንድሞቻችን በከተሞቻቸውና በመሰማሪያዎቻቸው ለሚቀመጡ ካህናትና ሌዋውያን ወደ እኛ ይሰበሰቡ ዘንድ እንላክ።
የእግዚአብሔርም ካህናት እንዳይሆኑ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አስለቅቀዋቸው ነበርና ሌዋውያን መሰምሪያቸውን ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
ክህነት ለሚገባቸው ለአሮን ልጆች ለካህናቱ፥ በከተሞቻቸውም ዙሪያ ባሉ መሰማሪያዎችና በሌሎችም ከተሞች ላሉ ለወንዶች ሁሉ፥ ከሌዋውያን ጋራ ለተቈጠሩ ሰዎችም ሁሉ ከፍለው ይሰጡ ዘንድ በስም የተጠሩ ሰዎች ነበሩ።
ለሌዋውያንም ፈንታቸው እንዳልተሰጠ፥ የሚያገለግሉትም ሌዋውያንና መዘምራን እያንዳንዱ ወደ እርሻው እንደ ሄደ ተመለከትሁ።
የሌዋውያን ርስት፥ የከተማዪቱም ይዞታ ለአለቃው በሆነው መካከል ይሆናል፤ በይሁዳ ድንበርና በብንያም ድንበር መካከል የአለቃው ዕጣ ክፍል ይሆናል።
“ከይሁዳም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለመባ የተለየ ክፍል ይሆናል፤ ወርዱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል፤ ርዝመቱም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ከዕጣ ክፍሎች እንደ አንዱ ይሆናል፤ ቤተ መቅደሱም በመካከሉ ይሆናል።
“አንድ ሌዋዊ ሰው ከሚቀመጥባቸው በእስራኤል ሁሉ ዘንድ ካሉት ከተሞች ከአንዲቱ፥ በፍጹም ልብም ሊያገለግል እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ቢመጣ፥