Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 13:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ዳዊ​ትም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጉባኤ ሁሉ፥ “መል​ካም መስሎ የታ​ያ​ችሁ እንደ ሆነ፥ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፈቅዶ እንደ ሆነ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ሀገር ሁሉ ለቀ​ሩት ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውና በመ​ሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ለሚ​ቀ​መጡ ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን ወደ እኛ ይሰ​በ​ሰቡ ዘንድ እን​ላክ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከዚያም ለመላው የእስራኤል ማኅበር እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ ነገሩ መልካም መስሎ ከታያችሁና የአምላካችን የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ፣ በእስራኤል ግዛት ሁሉ ለሚኖሩ በሩቅም ሆነ በቅርብ ላሉት ለቀሩት ወንድሞቻችን እንዲሁም በየራሳቸው ከተሞችና መሰማሪያዎች የሚኖሩ ካህናትና ሌዋውያን መጥተው ከእኛ ጋራ እንዲሰባሰቡ እንላክባቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ዳዊትም የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “መልካም መስሎ ቢታያችሁ፥ የጌታም የአምላካችን ፈቃድ ቢሆን፥ በእስራኤል አገር ሁሉ ለቀሩት ወንድሞቻችን በከተሞቻቸውና በመሰማሪያዎቻቸውም ለተቀመጡት ካህናትና ሌዋውያን ወደ እኛ እንዲሰበሰቡ እንላክባቸው፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከዚያም በኋላ ለመላው የእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ሲል አስታወቀ፥ “እናንተ ከተስማማችሁበትና የአምላካችን የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ፥ የቀሩት የአገራችን ሰዎች፥ ካህናትና ሌዋውያን ወደሚኖሩባቸው ታናናሽ ከተማዎች መልእክተኞች ልከን ወደዚህ መጥተው ከእኛ ጋር እንዲሰበሰቡ እንንገራቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ዳዊትም የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ “መልካም መስሎ የታያችሁ እንደ ሆነ፥ ከአምላካችን ከእግዚአብሔርም ወጥቶ እንደ ሆነ፥ በእስራኤል አገር ሁሉ ለቀሩት ወንድሞቻችን በከተሞቻቸውና በመሰማርያዎቻቸውም ለሚቀመጡ ካህናትና ሌዋውያን ወደ እኛ ይሰበሰቡ ዘንድ እንላክ፤

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 13:2
16 Referencias Cruzadas  

ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ተዋጉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ሸሹ፤ ተዋ​ግ​ተ​ውም በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ላይ ወደቁ።


ምና​ል​ባት በሕ​ያው አም​ላክ ላይ ይገ​ዳ​ደር ዘንድ ጌታው የአ​ሦር ንጉሥ የላ​ከ​ውን የራ​ፋ​ስ​ቂ​ስን ቃል አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰማ እንደ ሆነ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ሰማው ቃል ይገ​ሥ​ጸው እንደ ሆነ፥ ስለ​ዚህ ለቀ​ረው ቅሬታ ጸልይ” አሉት።


ማኅበርን የሚያከብሩ ማስተዋልን ገንዘብ ያደርጋሉ። ምክርም በመካሮች ልብ ትኖራለች።


በሸ​ለ​ቆ​ውም የነ​በ​ሩት የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ እስ​ራ​ኤል እንደ ሸሹ፥ ሳኦ​ልና ልጆ​ቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ለቅ​ቀው ሸሹ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም መጥ​ተው ተቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው።


ንጉሡ ኢዮ​ራም ግን ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል ጋር በተ​ዋጋ ጊዜ ሶር​ያ​ው​ያን ያቈ​ሰ​ሉ​ትን ቍስል ይታ​ከም ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ተመ​ልሶ ነበር። ኢዩም ከእ​ርሱ ጋር ለነ​በ​ሩት እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ከእኔ ጋር ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለሞት መስ​ጠት ትች​ላ​ላ​ች​ሁን? እን​ግ​ዲህ ማንም የሚ​ያ​መ​ል​ጣ​ችሁ፥ ከከ​ተ​ማ​ች​ሁም የሚ​ወጣ እን​ዳ​ይ​ኖ​ርና በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል እን​ዳ​ያ​ወራ ተጠ​ን​ቀቁ።”


እነ​ር​ሱም፥ “ለዚህ ሕዝብ አሁን አገ​ል​ጋይ ብት​ሆን፥ ብት​ገ​ዛ​ላ​ቸ​ውም፥ መል​ሰ​ህም በገ​ር​ነት ብት​ነ​ግ​ራ​ቸው፥ በዘ​መኑ ሁሉ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ይሆ​ኑ​ል​ሃል” ብለው ተና​ገ​ሩት።


ይህ​ንም ቃሌን ብታ​ደ​ርግ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያበ​ረ​ታ​ሃል፤ መፍ​ረ​ድም ትች​ላ​ለህ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በሰ​ላም ወደ ስፍ​ራው ይመ​ለ​ሳል።”


ዳዊ​ትም ከሻ​ለ​ቆ​ችና ከመቶ አለ​ቆች፥ ከአ​ለ​ቆ​ቹም ሁሉ ጋር ተማ​ከረ።


ከሳ​ኦ​ልም ዘመን ጀምሮ አል​ፈ​ለ​ጓ​ት​ምና የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ እኛ እን​መ​ል​ሳት” አላ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios