በከነዓን ምድርም ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ የእስራኤል ልጆች እንደ መጡ ሰማ።
በከነዓን በምትገኘው በኔጌብ የሚኖረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ፣ የእስራኤላውያንን መምጣት ሰማ።
በከነዓን ምድርም በደቡብ በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ የእስራኤል ልጆች እንደመጡ ሰማ።
በደቡብ ከነዓን በምትገኘው በዐራድ አገር የሚኖረው ከነዓናዊው የዐራድ ንጉሥ እስራኤላውያን መምጣታቸውን ሰማ።
በከነዓን ምድርም በደቡብ በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ የእስራኤል ልጆች እንደ መጡ ሰማ።
አብራምም ከዚያ ተነሣ፤ እየተጓዘም ወደ አዜብ ሄደ፤ በዚያም ኖረ።
አሮንም በሖር ተራራ ላይ በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሃያ ሦስት ዓመት ነበረ።
እነርሱም ከሖር ተራራ ተጕዘው በሴልሞና ሰፈሩ።