ዘኍል 33:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም አሮን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፤ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት፥ በአምስተኛው ወር፥ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ትእዛዝ ካህኑ አሮን ወደ ሖር ተራራ ወጣ፤ እዚያም እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ በአርባኛው ዓመት፣ በዐምስተኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም አሮን በጌታ ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፥ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑ አሮን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፤ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም አሮን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፥ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ። |
በአርባኛው ዓመት በዐሥራ አንደኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን፥ ሙሴ እንዲነግራቸው እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ያዘዘውን ሁሉ ለእስራኤል ልጆች ነገራቸው፤
“የእስራኤልም ልጆች የማስቢ ወገን ከሚሆን ከኢያቅም ልጆች ቦታ ከቤሮስ ተጓዙ። በዚያም አሮን ሞተ፤ ተቀበረም፤ በእርሱም ፋንታ ልጁ አልዓዛር ካህን ሆነ።
ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ እንደ ሞተ፥ ወደ ወገኖቹም እንደ ተጨመረ፥ በወጣህበት ተራራ ሙት፤ ወደ ወገኖችህም ተጨመር፤