ዘኍል 32:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለልጆቻችሁ ከተሞችን፥ ለበጎቻችሁም በረቶችን ሥሩ፤ ከአፋችሁም የወጣውን ነገር አድርጉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሴቶቻችሁና ለልጆቻችሁ ከተሞች፣ ለበግና ለፍየል መንጎቻችሁም ጕረኖች ሥሩላቸው፤ የገባችሁበትን የተስፋ ቃል ግን ፈጽሙ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለልጆቻችሁ ከተሞች፥ ለበጎቻችሁም በረቶች ሥሩ፤ ከአንደበታችሁም የወጣውን ቃል ፈጽሙ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ከተሞቻችሁንና ለእንስሶቻችሁ የሚሆኑትን በረቶች ሥሩ፤ ነገር ግን የገባችሁትንም የተስፋ ቃል ፈጽሙ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለልጆቻችሁ ከተሞች፥ ለበጎቻችሁም በረቶች ሥሩ፤ ከአፋችሁም የወጣውን ነገር አድርጉ። |
ሰው ሁሉ ለእግዚአብሔር ስእለት ቢሳል፥ ወይም መሐላን ቢምል፤ ራሱንም ቢለይ፥ ቃሉን አያርክስ፤ ከአፉ እንደ ወጣው ሁሉ ያድርግ።
የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆችም ሙሴን እንዲህ ብለው ተናገሩት፥ “እኛ አገልጋዮችህ ጌታችን እንዳዘዘ እናደርጋለን።