ዘኍል 31:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ባሪያዎችህ ወደ ሰልፍ የወጡትን ከእጃችን በታች ያሉትን ቈጠሩ፤ ከእኛም አንድ አልጐደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ አሉት፤ “እኛ አገልጋዮችህ በእጃችን ሥር ያሉትን ወታደሮች ቈጥረናል፤ አንድም የጐደለ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴንም እንዲህ አሉት፦ “እኛ ባርያዎችህ ወደ ጦርነት የወጡትን ከእጃችን በታች ያሉትን ቈጥረናል፥ ከእኛ አንድም ሰው አልጐደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኛ አገልጋዮችህ፥ በእኛ ትእዛዝ ሥር የነበሩትን ወታደሮች ሁሉ ቈጥረናል፤ ከእነርሱ አንድም የጐደለ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴንም፦ እኛ ባሪያዎችህ ወደ ሰልፍ የወጡትን ከእጃችን በታች ያሉትን ቈጠርን፥ ከእኛም አንድ አልጐደለም። |
“አንተ የእስራኤልን ልጆች ቍጥር የወሰድህ እንደ ሆነ በቈጠርሃቸው ጊዜ መቅሠፍት እንዳይሆንባቸው፥ በቈጠርሃቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ።
ሰውም ሁሉ ከአገኘው ከወርቅ ዕቃ፥ ከእግር አልቦም፥ ከአምባርም፥ ከቀለበትም ከጕትቻም፥ ከድሪውም ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ታስተሰርዩልን ዘንድ ለእግዚአብሔር መባ አምጥተናል” አሉት።