ዘኍል 31:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴ ከእስራኤል ልጆች ድርሻ ከሰውና ከእንስሳ ከሃምሳ አንድ ወሰደ፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ድንኳን ሥርዐት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ሰጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእስራኤላውያን እኩሌታ ድርሻ ላይ፣ ሙሴ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ከየዐምሳው ሰውና እንስሳ አንዳንድ መርጦ የእግዚአብሔርን ማደሪያ ድንኳን በኀላፊነት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእስራኤል ልጆች ድርሻ ሙሴ ከሰውና ከእንስሳ ከኀምሳ አንድ ወሰደ፥ ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው የጌታን ማደሪያ አገልግሎት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ሰጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም ድርሻ ሙሴ ከኀምሳው አንድ እስረኛ፥ ከኀምሳው አንድ እንስሳ ወስዶ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በእግዚአብሔር ድንኳን ላይ ኀላፊነት ላላቸው ለሌዋውያን ሰጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእስራኤል ልጆች ድርሻ ሙሴ ከሰውና ከእንስሳ ከአምሳ አንድ ወሰደ፥ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ማደሪያ አገልግሎት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ሰጠ። |
ነገር ግን በእስራኤል ልጆች ላይ ዕዳ እንዳይሆንባቸው ሌዋውያን በምስክሩ ድንኳን ዙሪያ ፊት ለፊት ይስፈሩ፤ ሌዋውያን የምስክሩን ድንኳን ሕግ ይጠብቁ።”
ከእስራኤልም ልጆች ድርሻ እኩሌታ፥ ከሰዎችም፥ ከበሬዎችም፥ ከበጎችም፥ ከአህዮችም፥ ከእንስሶችም ሁሉ ከአምሳ አንድ ትወስዳለህ፤ የእግዚአብሔርንም ድንኳን ሥርዐት ለሚጠብቁ ለሌዋውያን ትሰጣለህ።”
በዚያም ቀን ኢያሱ እነርሱን ለማኅበሩና ለእግዚአብሔር መሠዊያ እንጨት ቈራጮችና ውኃ ቀጂዎች አደረጋቸው። ስለዚህም የገባዖን ሰዎች ለማኅበሩና ለእግዚአብሔር መሠዊያ፥ እግዚአብሔርም ለመረጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ እንጨት ቈራጮች፥ ውኃም ቀጂዎች ሆኑ።